Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 3:33 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

33 በሜራሪ ውስጥ የሞሖላውያን ወገንና የሙሳያውያን ወገን ይካተቱ ነበር፤ የሜራሪ ወገኖች እነዚህ ናቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

33 የሞሖላውያንና የሙሳያውያን ጐሣዎች ከሜራሪ ወገን ናቸው፤ እነዚህም የሜራሪ ጐሣዎች ነበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

33 የማሕሊና የሙሺ ቤተሰቦች በሜራሪ ጐሣ ውስጥ ተጠቃለው ነበር። እነዚህ የሜራሪ ቤተሰቦች ናቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

33 ለሜ​ራሪ የሞ​ሖሊ ወገን የሙሲ ወገን ነበሩ፤ የሜ​ራሪ ወገ​ኖች እነ​ዚህ ናቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

33 ከሜራሪ የሞሖላውያን ወገን የሙሳያውያንም ወገን ነበሩ፤ የሜራሪ ወገኖች እነዚህ ናቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 3:33
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የሜራሪ ልጆች ሞሖሊና ሙሲ ነበሩ። የሞሖሊ ልጆች አልዓዛርና ቂስ ነበሩ።


የሜራሪ ልጆች፤ ሞሖሊና ሙሲ ነበሩ። የሌዋውያን ወገኖች በየአባቶቻቸው ቤቶች እነዚህ ናቸው።


እነዚህ የሌዊ ወገኖች ናቸው፤ የሊብናውያን ወገን፥ የኬብሮናውያን ወገን፥ የሞሖላውያን ወገን፥ የሙሳውያን ወገን፥ የቆሬያውያን ወገን። ቀዓትም እንበረምን ወለደ።


የሜራሪም ልጆች በየወገኖቻቸው፤ ሞሖሊ፥ ሙሲ። የሌዋውያን ወገኖች በየአባቶቻቸው ቤቶች እነዚህ ናቸው።


የሌዋውያንም አለቆች አለቃ የካህኑ የአሮን ልጅ አልዓዛር ይሆናል፤ እርሱም የመቅደሱን ግዴታ በሚፈጽሙት ላይ ተቆጣጣሪ ይሆናል።


ከእነርሱም ወንዶች ሁሉ እንደ ቁጥራቸው ዕድሜው አንድ ወር የሞላውና ከዚያም በላይ ያለው የተቈጠሩት ስድስት ሺህ ሁለት መቶ ነበሩ።


“የሜራሪንም ልጆች በየወገኖቻቸው በየአባቶቻቸውም ቤቶች ቁጠራቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች