Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 29:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 በሰባተኛውም ወር ከወሩ በመጀመሪያ ቀን የተቀደሰ ጉባኤ ይኑራችሁ፤ የጉልበት ሥራ ሁሉ አትሥሩበት፤ መለከቶች የሚነፉበት ቀን ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 “ ‘በሰባተኛው ወር በመጀመሪያው ቀን የተቀደሰ ጉባኤ አድርጉ፤ የዘወትር ሥራም አትሥሩበት፤ ይህም የመለከት ድምፅ የምታሰሙበት ቀናችሁ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 “ሰባተኛው ወር በገባ በመጀመሪያው ቀን ለማምለክ ትሰበሰባላችሁ፤ በእርሱም ምንም ሥራ አትሠሩበትም፤ በዚያን ቀን መለከት ይነፋል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 “በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ወር ከወሩ የመ​ጀ​መ​ሪ​ያዋ ቀን ለእ​ና​ንተ ይህች ዕለት የተ​ቀ​ደ​ሰች ናት፤ የተ​ግ​ባ​ርን ሥራ ሁሉ አት​ሥ​ሩ​ባት፤ ምል​ክት ያለ​ባት ቀን ትሁ​ን​ላ​ችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 በሰባተኛውም ወር ከወሩ በመጀመሪያ ቀን የተቀደሰ ጉባኤ ይሁንላችሁ፤ የተግባርን ሥራ ሁሉ አትሥሩበት፤ መለከቶች የሚነፉበት ቀን ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 29:1
21 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ጌታም በእነርሱ ላይ ይገለጣል፥ የአምላኩም ቀስት እንደ መብረቅ ይወጣል፤ እግዚአብሔር ጌታም መለከትን ይነፋል፥ ከደቡብም ዐውሎ ነፋስ ይመጣል።


በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፤ ታላቅ መለከት ይነፋል፥ በአሦርም የጠፉ፥ በግብጽ ምድርም የተሰደዱ ይመጣሉ፤ በተቀደሰውም ተራራ በኢየሩሳሌም ለጌታ ይሰግዳሉ።


የዙፋንህ መሠረት ጽድቅና ፍርድ፥ ምሕረትና እውነት በፊትህ ይሄዳሉ።


ከሰባተኛው ወር ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ለጌታ የሚቃጠል መሥዋዕት ማቅረብ ጀመሩ፤ ነገር ግን የጌታ መቅደስ አልተመሠረተም ነበር።


እንዲሁ እስራኤል ሁሉ ሆ እያሉ፥ ቀንደ መለከትና እምቢልታ እየነፉ፥ ጸናጽልና መሰንቆም በገናም እየመቱ፥ የጌታን የቃል ኪዳን ታቦት አመጡ።


ዝማሬውን አንሡ ከበሮንም ስጡ፥ ደስ የሚያሰኘውን በገና ከመሰንቆ ጋር፥


የመከር በዓል፥ በእርሻህ የዘራኸውን የፍሬህን በኵራት፥ ዓመቱም ሳያልቅ ፍሬህን ከእርሻ በምትሰበስብበት ጊዜ የመክተቻውን በዓል ጠብቅ።


የሰባቱን ሱባዔ በዓል ትጠብቃለህ፥ እርሱም የስንዴ መከር በኵራት ነው፤ በዓመቱም መጨረሻ የመክተቻ በዓል ታደርጋለህ።


ጌታም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦


“ደግሞ በበኵራት ቀን ከሰባቱ ሱባዔ በዓላችሁ አዲሱን የእህል ቁርባን ለጌታ ባቀረባችሁ ጊዜ፥ የተቀደሰ ጉባኤ ይኑራችሁ፤ የጉልበት ሥራ ሁሉ አትሥሩበት።


ለጌታ መዓዛው ያማረ ሽታ እንዲሆን የሚቃጠለውን መሥዋዕት፥ አንድ ወይፈን፥ አንድ አውራ በግ፥ ነውር የሌለባቸውን ሰባት የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች ታቀርባላችሁ፤


በሰባተኛውም ወር በዓሥራ አምስተኛው ቀን የተቀደሰ ጉባኤ ይኑራችሁ፤ የጉልበት ሥራ ሁሉ አትሥሩበት፥ ሰባት ቀንም ለጌታ በዓል አድርጋችሁ ታከብራላችሁ።


በመጀመሪያው ቀን የተቀደሰ ጉባኤ ይኑራችሁ፤ የጉልበት ሥራ ሁሉ አትሥሩበት።


“በስምንተኛውም ቀን የተቀደሰ ጉባኤ ይኑራችሁ፤ የጉልበት ሥራ ሁሉ አትሥሩበት።


ካህኑ ዕዝራ በሰባተኛው ወር በመጀመሪያው ቀን ሕጉን ወንዶች፥ ሴቶችና አስተውለው መስማት የሚችሉ ባሉበት በጉባኤው ሁሉ ፊት አመጣው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች