ዘኍል 28:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)2 የእስራኤልን ልጆች እንዲህ ብለህ እዘዛቸው፦ “‘ማዕዴን፥ ለእኔ መዓዛው ያማረ ሽታ እንዲሆን በእሳት የሚቀርበውን ቁርባኔን፥ መባዬን በተገቢው ጊዜ እንድታቀርቡልኝ በጥንቃቄ ልብ በሉ።’ ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም2 “ይህን ትእዛዝ ለእስራኤላውያን እንዲህ ብለህ ስጣቸው፤ ‘ሽታው ደስ እንዲያሠኘኝ በእሳት የሚቀርብልኝን የምግብ ቍርባን የተወሰነውን ጊዜ ጠብቃችሁ አቅርቡልኝ።’ ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም2 “ለእስራኤል ሕዝብ የምትሰጣቸው ትእዛዝ ይህ ነው፦ መዓዛው ደስ የሚያሰኝ በእሳት የሚቃጠል የምግብ ቊርባን እንዲያቀርቡልኝ ንገራቸው።” ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)2 “የእስራኤልን ልጆች እንዲህ ብለህ እዘዛቸው፦ ቍርባኔን፥ መባዬንና የበጎ መዓዛ መሥዋዕቴን በበዓላት ቀኖች ታቀርቡልኝ ዘንድ ጠብቁ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)2 የእስራኤልን ልጆች እንዲህ ብለህ እዘዛቸው፦ መብሌን፥ ለእኔ ጣፋጭ ሽታ እንዲሆን በእሳት የተደረገውን ቍርባኔን፥ መባዬን በየጊዜው ታቀርቡልኝ ዘንድ ጠብቁ። ምዕራፉን ተመልከት |