Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 26:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 በየወገናቸው የይሁዳም ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ከሴሎም የሴሎማውያን ወገን፥ ከፋሬስ የፋሬሳውያን ወገን፥ ከዛራ የዛራውያን ወገን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 የይሁዳ ዘሮች በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤ በሴሎም በኩል፣ የሴሎማውያን ጐሣ፤ በፋሬስ በኩል፣ የፋሬሳውያን ጐሣ፤ በዛራ በኩል፣ የዛራውያን ጐሣ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 የቀሩት የይሁዳ ልጆች ሴሎም ፋሬስ ዛራና ተወላጆቻቸው ናቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ከያ​ሱብ የያ​ሱ​ባ​ው​ያን ወገን፥ ከሥ​ምራ የሥ​ም​ራ​ው​ያን ወገን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 የይሁዳም ልጆች በየወገናቸው፤ ከሴሎም የሴሎማውያን ወገን፥ ከፋሬስ የፋሬሳውያን ወገን፥ ከዛራ የዛራውያን ወገን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 26:20
18 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከዚያም ይሁዳ ምራቱን ትዕማርን፥ “ልጄ ሴሎም ለአካለ መጠን እስኪደርስ ድረስ ወደ አባትሽ ቤት ሄደሽ መበለት ሆነሽ ብትኖሪ ይሻላል” አላት፤ ይህን ያለውም፥ ሴሎም እንደ ወንድሞቹ ተቀሥፎ ይሞትብኛል ብሎ ስለ ሠጋ ነበር። ትዕማርም እንዳላት ሄደች፤ በአባቷም ቤት ተቀመጠች።


የመበለትነት ልብሷን አውልቃ፥ ማንነቷ እንዳይታወቅ ፊቷን በሻሽ ተከናንባ ወደ ተምና በሚወስደው መንገድ ዳር ባለች ኤናይም በተባለች ከተማ መግቢያ ላይ ተቀመጠች፤ ይህን ያደረገችው፥ ሴሎም ለአካለ መጠን ቢደርስም፥ እርሷን እንዲያገባ አባቱ አለመፈለጉን ስላወቀች ነው።


አሁንም ደግማ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙንም ሴሎም ብላ አወጣችለት፤ እርሱንም የወለደችው ክዚብ በተባለ ቦታ ነበር።


የይሁዳም ልጆች፥ ዔር፥ ኦውናን፥ ሴላ፥ ፋሬስ፥ ዛራሕ፥ ዔርና አውናን በከነዓን ምድር ሞቱ፥ የፋሬስም ልጆች ኤስሮም፥ ሐሙል።


ይሁዳ፥ ወንድሞችህ አንተን ያመሰግኑሃል፥ እጅህ በጠላቶችህ ደንደስ ላይ ነው፥ የአባትህ ልጆች በፊትህ ይሰግዳሉ።


የይሁዳም ልጅ የሴሎም ልጆች የሌካ አባት ዔር፥ የመሪሳ አባት ለዓዳ፥ ከአሽቤዓ-ቤት የሚሆኑ ጥሩ በፍታ የሚሠሩ ወገኖች፥


ከይሁዳ ልጅ ከፋሬስ ልጆች የባኒ ልጅ የአምሪ ልጅ የዖምሪ ልጅ የዓሚሁድ ልጅ ዑታይ ደግሞ በዚያ ተቀመጠ።


ከሴሎናውያንም በኩሩ ዓሣያና ልጆቹ በዚያ ተቀመጡ።


ከይሁዳ ልጅ ከዜራሕ ወገኖች የምሼዛቤል ልጅ፥ ፕታሕያ ሕዝቡን በሚመለከት ጉዳይ ሁሉ በንጉሡ አጠገብ ነበረ።


ከይሁዳ ልጆችና ከብንያም ልጆች የተወሰኑት በኢየሩሳሌም ተቀመጡ። ከይሁዳ ልጆች፦ ከፋሬስ ልጆች የማሃላልኤል ልጅ፥ የሽፋጥያ ልጅ፥ የአማርያ ልጅ፥ የዘካርያስ ልጅ፥ የዑዚያ ልጅ ዓታያ፤


በኢየሩሳሌም የተቀመጡት የፋሬስ ልጆች ሁሉ አራት መቶ ስድሳ ስምንት ኃያላን ነበሩ።


የፋሬስም ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ከኤስሮም የኤስሮማውያን ወገን፥ ከሐሙል የሐሙላውያን ወገን።


ይሁዳም ከትዕማር ፋሬስንና ዛራን ወለደ፤ ፋሬስ ኤስሮምን ወለደ፤ ኤስሮም አራምን ወለደ፤


የአሚናዳብ ልጅ፥ የአራም ልጅ፥ የአሮኒ ልጅ፥ የኤስሮም ልጅ፥ የፋሬስ ልጅ፥ የይሁዳ ልጅ፥


ከይሁዳ ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ ታተሙ፤ ከሮቤል ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ፥ ከጋድ ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ፥


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች