Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 21:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “እባብን ሠርተህ በእንጨት ላይ ስቀል፤ የተነደፈውም ሁሉ ሲያየው በሕይወት ይኖራል።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 እግዚአብሔር ሙሴን፣ “እባብ ሠርተህ በዕንጨት ላይ ስቀለው፤ የተነደፈውም ሁሉ ወደ እርሱ በማየት ይድናል” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 በዚያን ጊዜ እግዚአብሔር ሙሴን “አንድ የነሐስ እባብ ሠርተህ በረዥም ትክል እንጨት ላይ ስቀለው፤ በእባብ የተነከሰ ሁሉ እርሱን በሚያይበት ጊዜ ይድናል” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “የናስ እባ​ብን ሠር​ተህ በዓ​ላማ ላይ ስቀል፤ እባ​ቡም ሰውን ቢነ​ድፍ የተ​ነ​ደ​ፈው ሁሉ ይመ​ል​ከ​ተው፤ ይድ​ና​ልም” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ሙሴም ስለ ሕዝቡ ጸለየ። እግዚአብሔርም ሙሴን፦ እባብን ሠርተህ በዓላማ ላይ ስቀል፤ የተነደፈውም ሁሉ ሲያያት በሕይወት ይኖራል አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 21:8
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የአሕዛብን የማምለኪያ ስፍራዎችን ደመሰሰ፤ የድንጋይ ዐምዶችን ሰባበረ፤ አሼራ ተብላ በምትጠራው ሴት አምላክ ስም የተቀረጹትን ምስሎች ሁሉ አንኮታክቶ ጣለ፤ ሙሴ ከነሐስ ሠርቶት የነበረውን ኔሑሽታን ተብሎ የሚጠራውን የእባብ ምስል ሰባብሮ አደቀቀ፤ እስከዚያን ጊዜ ድረስ ግን እስራኤላውያን ለእርሱ ዕጣን ያጥኑለት ነበር።


ጌታ ርኅሩኅና መሓሪ ነው፥ ከቁጣ የራቀ፥ ጽኑ ፍቅሩም ብዙ ነው፥


ፍልስጥኤም ሆይ፥ ከእባቡ ሥር እፉኝት ይወጣልና፥ ፍሬውም የሚበርርና እሳት የሚመስል እባብ ይሆናልና የመታሽ በትር ስለ ተሰበረ ሁላችሁም ደስ አይበላችሁ።


በደቡብ ስላሉ እንስሶች የተነገረ ራእይ። ተባትና እንስት፥ አንበሳ እፉኝትም፥ ተወርዋሪ እባብም በሚወጡባት፥ በመከራና በጭንቀት ምድር በኩል፥ ብልጥግናቸውን በአህዮች ጫንቃ ላይ፥ መዛግብቶቻቸውንም በግመሎች ሻኛ ላይ እየጫኑ ወደማይጠቅሟቸው ሕዝብ ይሄዳሉ።


እናንተ የምድር ዳርቻ ሁሉ፥ እኔ አምላክ ነኝና፥ ከእኔም በቀር ሌላ የለምና ወደ እኔ ዘወር በሉ ትድኑማላችሁ።


ሙሴም በምድረ በዳ እባብን እንደ ሰቀለ እንዲሁ የሰው ልጅም መሰቀል ይገባዋል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች