ዘኍል 20:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)6 ሙሴና አሮንም ከጉባኤው ፊት ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ሂደው በግምባራቸው ወድቀው ሰገዱ፤ የጌታም ክብር ተገለጠላቸው። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም6 ሙሴና አሮን ከማኅበረ ሰቡ ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ሄደው በግንባራቸው ተደፉ፤ የእግዚአብሔርም ክብር ተገለጠላቸው። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም6 ሙሴና አሮን ከሕዝቡ ፈቅ ብለው ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ሄዱ፤ በግንባራቸው ወደ መሬት ተደፍተው ሳሉም የእግዚአብሔር ክብር ተገለጠላቸው። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)6 ሙሴና አሮንም ከማኅበሩ ፊት ወደ ምስክሩ ድንኳን ዳጃፍ ሄደው በግንባራቸው ወደቁ፤ የእግዚአብሔርም ክብር ተገለጠላቸው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)6 ሙሴና አሮንም ከጉባኤው ፊት ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ሂደው በግምባራቸው ወደቁ፤ የእግዚአብሔርም ክብር ተገለጠላቸው። ምዕራፉን ተመልከት |