Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 17:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ፈጽሞ ወደ ጌታ ማደሪያ የሚቀርብ ሁሉ፥ ይሞታል፤ በውኑ ሁላችን እንሞታለንን?”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ወደ እግዚአብሔር ማደሪያ የሚጠጋ እንኳ ማንኛውም ሰው ቢሆን ይሞታል፤ ሁላችንም ልንጠፋ ነው እንዴ?”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ወደ ድንኳኑ የሚቀርብ ሁሉ የሚሞት ከሆነ ሁላችንም እንጠፋለን ማለት ነውን?”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ድን​ኳን የሚ​ነካ ሁሉ ይሞ​ታል። በውኑ ሁላ​ችን ፈጽ​መን እን​ሞ​ታ​ለን?”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 የሚቀርብ ሁሉ፥ ወደ እግዚአብሔር ማደሪያ የሚቀርብ፥ ይሞታል፤ በውኑ ሁላችን እንሞታለንን? ብለው ተናገሩት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 17:13
21 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ነገር ግን እግዚአብሔር ‘በገነት መካከል ካለው ከዛፉ ፍሬ፥ እንዳትሞቱ ከእርሱ አትብሉ፥ አትንኩትም።’” ብሏል።


በዚያም ዳዊት ለጌታ መሠዊያ ሠራ፤ የሚቃጠል መሥዋዕትና የሰላም መሥዋዕት አቀረበ። ከዚያም ጌታ ለምድሪቱ የቀረበውን ጸሎት ሰማ፤ በእስራኤል ላይ የመጣውም መቅሰፍት ቆመ።


ቀድሞም አልተሸከማችሁትምና፥ እንደ ሥርዓቱም አልፈለግነውምና ጌታ አምላካችን በመካከላችን ቊጣውን አወረደ።”


እኛ በቁጣህ አልቀናልና፥ በመዓትህም ደንግጠናልና።


አሁንም በምድር ሁሉ ላይ የሚጸናውን የጥፋት ትእዛዝ ከሠራዊት ጌታ ከእግዚአብሔር ዘንድ ሰምቻለሁና እስራት እንዳይጸናባችሁ አታፊዙ።


እርሱም ለማኅበሩ እንዲህ ብሎ ተናገረ፦ “እባካችሁ፥ ከእነዚህ ክፉዎች ድንኳን ርቃችሁ ገለል በሉ፤ በኃጢአታቸውም ሁሉ እንዳትጠፉ የእነርሱ የሆነውን ሁሉ አትንኩ።”


ጌታም አሮንን እንዲህ አለው፦ “አንተ ከአንተም ጋር ልጆችህና የአባቶችህ ቤት ከመቅደሱ ጋር በተገናኘ የሚፈጸምን በደል ትሸከማላችሁ፤ አንተም ከአንተም ጋር ልጆችህ ከክህነታችሁ ጋር በተገናኘ የሚፈጸምን በደል ትሸከማላችሁ።


ያንንም የእስራኤልን ሰው ተከትሎ ወደ ድንኳኑ ገባ። እስራኤላዊውንም ሰውና ሴቲቱን ሁለቱንም ሆዳቸውን ወጋቸው። ከእስራኤልም ልጆች መቅሠፍቱ ተከለከለ።


የጌታም ቁጣ በእስራኤል ላይ ነደደ፥ በጌታም ፊት ክፉ ያደረገ ትውልድ ሁሉ እስኪጠፋ ድረስ አርባ ዓመት በምድረ በዳ ውስጥ አቅበዘበዛቸው።


ሐናንያም ይህን ቃል ሰምቶ ወደቀ፤ ሞተም፤ በሰሙትም ሁሉ ላይ ታላቅ ፍርሃት ሆነ።


አሁን ግን እናንተ በፊት ርቃችሁ የነበራችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ ሆናችሁ በክርስቶስ ደም ቀርባችኋል።


“እንዲህም ሆነ፥ ጦረኞቹ ከጠፉ ከሕዝቡም መካከል ከሞቱ በኋላ፥


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች