ዘኍል 16:47 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)47 አሮንም ሙሴ እንደ ተናገረው ጥናውን ወስዶ ወደ ጉባኤው መካከል ሮጠ፤ እነሆም፥ መቅሠፍቱ በሕዝቡ መካከል ጀምሮ ነበር፤ ዕጣንም ጨመረ፥ ለሕዝቡም አስተሰረየላቸው። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም47 ስለዚህ አሮን፣ ሙሴ በነገረው መሠረት ወደ ማኅበሩ መካከል ሮጦ ገባ፤ መቅሠፍቱም ቀደም ብሎ በሕዝቡ መካከል መስፋፋት ጀምሮ ነበር፤ ሆኖም አሮን ዕጣኑን ዐጥኖ አስተሰረየላቸው። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም47 አሮንም በመታዘዝ ጥናውን ይዞ ወደ ተሰበሰበው ሕዝብ መካከል ፈጥኖ ሄደ፤ መቅሠፍቱ እንደ ጀመረ በተመለከተ ጊዜ ዕጣኑን በፍሙ ላይ አድርጎ ለሕዝቡ አስተሰረየላቸው፤ ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)47 አሮንም ሙሴ እንደ ተናገረው ጥናውን ወስዶ ወደ ማኅበሩ መካከል ፈጥኖ ሮጠ፤ እነሆም፥ መቅሠፍቱ በሕዝቡ መካከል ጀምሮ ነበር፤ ዕጣንም ጨመረ፤ ለሕዝቡም አስተሰረየላቸው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)47 አሮንም ሙሴ እንደ ተናገረው ጥናውን ወስዶ ወደ ጉባኤው መካከል ሮጠ፤ እነሆም፥ መቅሠፍቱ በሕዝቡ መካከል ጀምሮ ነበር፤ ዕጣንም ጨመረ፥ ለሕዝቡም አስተሰረየላቸው። ምዕራፉን ተመልከት |