ዘኍል 16:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)17 ሁላችሁም ጥናዎቻችሁን ውሰዱ፥ ዕጣንም አድርጉባቸው፥ እያንዳንዳችሁም ጥናዎቻችሁን ወደ ጌታ ፊት አምጡ፥ ሁለት መቶ ኀምሳ ጥናዎች፤ አንተም እንዲሁም አሮን እያንዳንዳችሁ ጥናዎቻችሁን አምጡ።” ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም17 እያንዳንዱም ሰው ጥናውን ይወስዳል፤ በአጠቃላይ ሁለት መቶ ዐምሳ ጥናዎች ይሆናሉ፤ በዚያም ላይ ዕጣን ጨምሮ በእግዚአብሔር ፊት ያቀርባል፤ አንተና አሮንም ጥናዎቻችሁን እንደዚሁ ታቀርባላችሁ።” ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም17 እያንዳንዳችሁ ጥናችሁን ይዛችሁ ኑ፤ በውስጡም ዕጣን ጨምሩበት፤ ከሁለት መቶ ኀምሳ ጥናዎች ጋር ወደ እግዚአብሔር ፊት ዕጣናችሁን ታቀርባላችሁ፤ አንተና አሮንም ዕጣናችሁን ታቀርባላችሁ።” ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)17 ሁላችሁም ጥናዎቻችሁን ውሰዱ፤ ዕጣንም አድርጉባቸው፤ እያንዳንዳችሁም ሁለት መቶ አምሳ ጥናዎቻችሁን ወደ እግዚአብሔር ፊት አምጡ፤ አንተ ደግሞ አሮንም ጥናዎቻችሁን አምጡ” አለው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)17 ሁላችሁም ጥናዎቻችሁን ውሰዱ፥ ዕጣንም አድርጉባቸው፥ እያንዳንዳችሁም ጥናዎቻችሁን ወደ እግዚአብሔር ፊት አምጡ፥ ሁለት መቶ አምሳ ጥናዎች፤ አንተ ደግሞ አሮንም ጥናዎቻችሁን አምጡ አለው። ምዕራፉን ተመልከት |