ዘኍል 15:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)24 ይህንንም ነገር ማኅበሩ ሳያውቀው በስሕተት የተደረገ ቢሆን፥ ማኅበሩ ሁሉ ለሚቃጠል መሥዋዕት ከእህሉ ቁርባንና ከመጠጡ ቁርባን ጋር እንደ ሕጉ ለጌታ መዓዛው ያማረ ሽታ እንዲሆን አንድ ወይፈን፥ ለኃጢአትም መሥዋዕት አንድ አውራ ፍየል ያቅርብ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም24 ይህም የተፈጸመው ሆነ ተብሎ ሳይሆንና ማኅበረ ሰቡም ሳያውቀው ከሆነ፣ ማኅበረ ሰቡ በሙሉ ሽታው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ አድርጎ አንድ ወይፈን በእሳት ለሚቃጠል መሥዋዕት ያቅርብ፤ ከዚሁም ጋራ ሥርዐቱ የሚጠይቀውን የእህል ቍርባንና የመጠጥ ቍርባን ደግሞም ለኀጢአት መሥዋዕት ተባዕት ፍየል ያቅርብ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም24 እንዲህ ዐይነቱ ስሕተት የተፈጸመው በማኅበሩ አለማወቅ ከሆነ አንድ ወይፈን አምጥተው መዓዛው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ የሚቃጠል መሥዋዕት አድርገው ያቅርቡት፤ ከእርሱም ጋር ተገቢውን የእህልና የወይን ጠጅ ቊርባን ያቅርቡ፤ በተጨማሪም አንድ ተባዕት ፍየል ስለ ኃጢአት ስርየት መሥዋዕት አድርገው ያቅርቡ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)24 በማኅበሩም ፊት ያልታወቀ ኀጢአት ቢኖር፥ ማኅበሩ ሁሉ ለሚቃጠል መሥዋዕትና ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ እንዲሆን ከመንጋዎች አንድ ንጹሕ ወይፈን ያቀርባሉ። የእህሉ ቍርባንና የመጠጡ ቍርባንም እንደ ሕጉ ነው፤ ለኀጢአትም መሥዋዕት አንድ አውራ ፍየል ያቀርባሉ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)24 ማኅበሩ ሳያውቁ በስሕተት ቢደረግ፥ ማኅበሩ ሁሉ ለሚቃጠል መሥዋዕት ከእህሉ ቍርባንና ከመጠጡ ቍርባን ጋር እንደ ሕጉ ለእግዚአብሔር ጣፋጭ ሽታ እንዲሆን አንድ ወይፈን፥ ለኃጢአትም መሥዋዕት አንድ አውራ ፍየል ያቀርባሉ። ምዕራፉን ተመልከት |