Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 14:28 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 እንዲህ በላቸው፦ ‘እኔ ሕያው ነኝና በጆሮዬ እንደ ተናገራችሁት እንዲሁ በእውነት አደርግባችኋለሁ፥ ይላል ጌታ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 ስለዚህ እንዲህ በላቸው፤ ‘እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ እኔ ሕያው ነኝ፤ ስትናገሩ የሰማኋችሁን እነዚያን ነገሮች አደርግባችኋለሁ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 እነሆ! ይህን መልስ ስጣቸው፥ ‘በጠየቃችሁት ዐይነት እንደማደርግባችሁ ሕያው በሆነ ስሜ እምላለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 እን​ዲህ በላ​ቸው፦ እኔ ሕያው ነኝና በጆ​ሮዬ እንደ ተና​ገ​ራ​ች​ሁት እን​ዲሁ በእ​ው​ነት አደ​ር​ግ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 እንዲህ በላቸው፦ እኔ ሕያው ነኝና በጆሮዬ እንደ ተናገራችሁት እንዲሁ በእውነት አደርግባችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 14:28
18 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዐይኖቻቸው ጥፋታቸውን ይዩ፥ ሁሉን ከሚችል አምላክ ቁጣ ይጠጡ።


በምድረ በዳም ይጥላቸው ዘንድ፥ ዘራቸውንም በአሕዛብ መካከል ይጥል ዘንድ፥ በየአገሩም ይበትናቸው ዘንድ፥ እጁን አነሣባቸው።


“ወደ ዕረፍቴም ጨርሶ አትገቡም” ስል በቁጣዬ ማልሁ።


ነገር ግን እኔ ጌታ የምናገረውን ቃል እናገራለሁ፥ ይፈጸማልም፥ ደግሞም አይዘገይም፥ እናንተ ዓመፀኛ ቤት ሆይ፥ በዘመናችሁ ቃሌን እናገራለሁ እፈጽመዋለሁም፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


ሕዝቡም ስለ ደረሰባቸው መከራ በጌታ ላይ አጉረመረሙ፤ ጌታም ሰምቶ እጅግ ተቈጣ፤ የጌታም እሳት በመካከላቸው ነደደ፥ የሰፈሩንም ዳር በላ።


የእስራኤልም ልጆች ሁሉ በሙሴና በአሮን ላይ አጉረመረሙ፤ ማኅበሩም ሁሉ እንዲህ አሉአቸው፦ “በግብጽ ምድር ሳለን ምነው በሞትን ኖሮ! ወይም በዚህ ምድረ በዳ ምነው በሞትን ኖሮ!


ነገር ግን እኔ ሕያው ነኝና በእውነት የጌታ ክብር ምድርን ሁሉ ይሞላል።


በእውነት ለአባቶቻቸው የማልሁላቸውን ምድር አያዩም፥ እነዚህም የናቁኝ ሰዎች ሁሉ አያይዋትም፤


ሙሴም እነዚህን ቃላት ለእስራኤል ልጆች ሁሉ ተናገረ፥ ሕዝቡም እጅግ አዘኑ።


‘ከግብጽ የወጡት ዕድሜአቸው ሀያ ዓመት የሞላቸውና ከዚያም በላይ ያሉት ሰዎች እኔን ፈጽመው አልተከተሉምና ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም ለመስጠት የማልሁላቸውን ምድር አያዩም፤


“ጌታም የቃላችሁን ድምፅ ሰምቶ ተቆጣም፤ እንዲህም ሲል ማለ፦


‘ከዚህ ክፉ ትውልድ፥ ከእነዚህ ሰዎች አንዳቸውም፥ ለአባቶቻችሁ እሰጣት ዘንድ የማልሁላቸውን መልካሚቱን ምድር አያይም፤


የዘሬድንም ፈፋ እስከ ተሻገርንበት ድረስ፥ ጌታ እንደ ማለባቸው የጦረኞች ትውልድ ሁሉ ከሰፈሩ መካከል እስከ ጠፉ ድረስ፥ ከቃዴስ በርኔ የተጓዝንበት ዘመን ሠላሳ ስምንት ዓመት ሆነ።


ከሰፈሩበትም መካከል አልቀው እስኪጠፉ ድረስ የጌታ እጅ በላያቸው ነበረ።


እጄን ወደ ሰማይ ዘርግቼ፥ ለዘለዓለም እኔ ሕያው እንደሆንኩ፥ እምላለሁ።


አርባ ዓመትስ የተቆጣባቸው እነማን ነበሩ? ሬሳቸው በምድረ በዳ የወደቀ፥ ኃጢአትን ያደረጉት እነርሱ አይደሉምን?


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች