ዘኍል 14:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)14 ለዚችም ምድር ሰዎች ይናገራሉ። አቤቱ፥ አንተ በዚህ ሕዝብ መካከል እንደሆንህ ሰምተዋል፤ አንተም፥ አቤቱ፥ ፊት ለፊት ተገልጠሃል፥ ደመናህም በላያቸው ቆሞአል፥ በቀንም በደመና ዓምድ፥ በሌሊትም በእሳት ዓምድ በፊታቸው ትሄዳለህ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም14 የተደረገውንም በዚች ምድር ለሚኖሩት ሰዎች ይነግሯቸዋል። እግዚአብሔር ሆይ፣ አንተ ከዚህ ሕዝብ ጋራ መሆንህን፣ ደግሞም አንተ እግዚአብሔር ሆይ፤ ፊት ለፊት እንደ ታየህና ደመናህ በላያቸው እንደ ሆነ፣ አንተም ቀን በደመና ዐምድ ሌሊትም በእሳት ዐምድ እፊት እፊታቸው እየሄድህ እንደ መራሃቸው ቀድሞውኑ ሰምተዋል። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም14 የሆነውን ሁሉ በዚህ ምድር ለሚኖሩት ሕዝቦች ይነግራሉ፤ እነዚህ ሕዝቦች አንተ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር መሆንህንና ደመናህ በላያችን በረበበ ጊዜ በግልጥ እንደምትታይ፥ ቀን በደመና ዐምድ፥ ሌሊት በእሳት ዐምድ እፊት እፊታችን እየሄድክ እንደምትመራን ከሰሙ ቈይተዋል። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)14 የዚያች ምድር ሰዎች፥ አንተ እግዚአብሔር በዚህ ሕዝብህ መካከል እንደ ሆንህ ሰምተዋል፤ አንተም፥ አቤቱ፥ ዐይን በዐይን እንደሚተያይ ተገልጠህላቸዋል። ደመናህም በላያቸው ቆመች። በቀንም በደመና ዐምድ ፥ በሌሊትም በእሳት ዐምድ በፊታቸው ትሄዳለህ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)14 ለዚችም ምድር ሰዎች ይናገራሉ። አንተ እግዚአብሔር በዚህ ሕዝብ መካከል እንደ ሆንህ ሰምተዋል፤ አንተም፥ አቤቱ፥ ፊት ለፊት ተገልጠሃል፥ ደመናህም በላያቸው ቆሞአል፥ በቀንም በደመና ዓምድ፥ በሌሊትም በእሳት ዓምድ በፊታቸው ትሄዳለህ። ምዕራፉን ተመልከት |