ዘኍል 13:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)20 ምድሪቱም ለም ወይም መካን፥ ዛፍ ያለባት ወይም የሌለባት እንደ ሆነች ተመልከቱ፤ ከምድሪቱ ፍሬ አምጡ፤ አይዞአችሁ።” በዚያን ጊዜም ወይኑ አስቀድሞ ፍሬ የሚያፈራበት ወቅት ነበረ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም20 ዐፈሩስ እንዴት ያለ ነው? ለም ወይስ ደረቅ? ደናም ወይስ ደን አልቦ? በተቻለ መጠን ከምድሪቱ በኵር ፍሬ ይዛችሁ ኑ።” ወቅቱ የወይን ፍሬ መብሰል የጀመረበት ጊዜ ነበር። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም20 አፈሩ ለም፥ ምድሪቱም በደን የተሸፈነች መሆንዋን መርምሩ፤ አይዞአችሁ እዚያ ከሚገኘው ፍራፍሬ ይዛችሁ ኑ።” ወቅቱም የወይን ፍሬ መብሰል የጀመረበት ጊዜ ነበር። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)20 ምድሪቱም ለም ወይም ጠፍ፥ ዛፍ ያለባት ወይም የሌለባት እንደ ሆነች አይታችሁ፥ ከምድሪቱ ፍሬ አምጡ፤” ወራቱም ወይኑ አስቀድሞ ፍሬ የሚያፈራበት ነበረ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)20 ምድሪቱም ወፍራም ወይም ስስ፥ ዛፍ ያለባት ወይም የሌለባት እንደ ሆነች እዩ፤ ከምድሪቱ ፍሬ አምጡ፤ አይዞአችሁ። በዚያን ጊዜም ወይኑ አስቀድሞ ፍሬ የሚያፈራበት ወራት ነበረ። ምዕራፉን ተመልከት |