ዘኍል 1:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)18 በሁለተኛውም ወር በመጀመሪያው ቀን ማኅበሩን ሁሉ ሰብሰቡአቸው፤ እነርሱም ዕድሜው ሀያ ዓመት የሆነውንና ከዚያም በላይ ያለውን አንድ በአንድ እንደየስማቸው ቍጥር፥ በየወገኖቻቸው በየአባቶቻቸውም ቤቶች ትውልዳቸውን መዘገቡ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም18 ከዚያም በሁለተኛው ወር በመጀመሪያው ቀን ማኅበረ ሰቡን በሙሉ በአንድነት ሰበሰቧቸው። የተሰበሰቡትም በየጐሣቸውና በየቤተ ሰባቸው የትውልድ ሐረጋቸውን ተናገሩ፤ ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም18 ሁለተኛው ወር በገባ በመጀመሪያው ቀን፥ ማኅበሩን ሁሉ በአንድነት ሰብስበው በየነገዱና በየቤተሰቡ ከመደቡ በኋላ የሕዝብ ቈጠራ አደረጉ፤ ዕድሜአቸው ኻያ ዓመትና ከዚያም በላይ የሆኑ ወንዶች ሁሉ እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት ስማቸው እየተመዘገበ ተቈጠሩ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)18 በሁለተኛው ዓመት በሁለተኛውም ወር በመጀመሪያው ቀን ማኅበሩን ሁሉ ሰበሰቡአቸው፤ ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚያም በላይ ያለውን ወንድ ሁሉ በየራሱ፥ በየወገኑም፥ በየአባቶቻቸውም ቤቶች፥ በየስማቸው ቍጥር ትውልዳቸውን ተናገሩ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)18 በሁለተኛውም ወር በመጀመሪያው ቀን ማኅበሩን ሁሉ ሰብሰቡአቸው፤ ከሀያ ዓመት ጀምሮ ከዚያም በላይ ያለውን በየራሱ በየወገኑም በየአባቶቻቸውም ቤቶች በየስማቸው ቍጥር ትውልዳቸውን ተናገሩ። ምዕራፉን ተመልከት |