Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ነህምያ 9:30 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 ነገር ግን ብዙ ዓመታት ታገሥሃቸው፥ በነቢያትህም እጅ በመንፈስህ መሰከርክባቸው፥ አላደመጡም፥ ስለዚህም በምድር አሕዛብ እጅ አሳልፈህ ሰጠሃቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 ብዙ ዘመን ታገሥሃቸው፤ በነቢያትህ አማካይነት በመንፈስህ አስጠነቀቅሃቸው። ነገር ግን አላደመጡህም፤ ከዚህም የተነሣ ጎረቤቶቻቸው ለሆኑ አሕዛብ አሳልፈህ ሰጠሃቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 አንተም ለብዙ ዓመቶች ታገሥካቸው፤ ያስተምሩአቸውም ዘንድ ነቢያትን በመንፈስህ አስነሣህላቸው፤ ነገር ግን እነርሱ አላዳመጡም፤ ስለዚህም ለጐረቤት ሕዝቦች ድል እንዲነሡአቸው አሳልፈህ ሰጠሃቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 ነገር ግን ብዙ ዓመ​ታት ታገ​ሥ​ሃ​ቸው፤ በነ​ቢ​ያ​ት​ህም እጅ በመ​ን​ፈ​ስህ መሰ​ከ​ር​ህ​ባ​ቸው፤ አላ​ደ​መ​ጡም፤ ስለ​ዚ​ህም በም​ድር አሕ​ዛብ እጅ አሳ​ል​ፈህ ሰጠ​ሃ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 ነገር ግን ብዙ ዓመታት ታገሥሃቸው፥ በነቢያትህም እጅ በመንፈስህ መሰከርህባቸው፥ አላደመጡም፥ ስለዚህም በምድር አሕዛብ እጅ አሳልፈህ ሰጠሃቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ነህምያ 9:30
34 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ወይስ የቸርነቱን፥ የቻይነቱን፥ የታጋሽነቱንም ባለጠግነት ትንቃለህን? የእግዚአብሔር ቸርነት ወደ ንስሓ ሊመራህ እንደሆነ አታውቅምን?


“እናንተ አንገተ ደንዳኖች ልባችሁና ጆሮአችሁም ያልተገረዘ፤ እናንተ ሁልጊዜ መንፈስ ቅዱስን ትቃወማላችሁ፤ አባቶቻችሁ እንደ ተቃወሙት እናንተ ደግሞ።


ያዕቆብን ለማረኩ እስራኤልንም ለበዘበዙ ሰዎች የሰጠ ማን ነው? እኛ የበደልነው፥ እነርሱም በመንገዱ ለመሄድ ያልወደዱት፥ ለሕጉም ያልታዘዙለት ጌታ እርሱ አይደለምን?


ማንኛውም ትንቢት በሰው ፈቃድ ከቶ አልመጣም፤ ነገር ግን ትንቢት በመንፈስ ቅዱስ የተመሩ ሰዎች ከእግዚአብሔር ተቀብለው ተናገሩ።


በእነርሱ ውስጥ የነበረው የክርስቶስ መንፈስ፥ ስለ ክርስቶስ መከራ እና ከእርሱም በኋላ ስለሚመጣው ክብር አስቀድሞ ሲመሰክር፥ ምን ወይም እንዴት ባለ ዘመን እንዳመለከተ ይመረምሩ ነበር።


እኔ ስጠራቸው እነርሱ አልሰሙኝም፥ እንዲሁ እነርሱ በሚጠሩኝ ጊዜ እኔ አልሰማቸውም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ።


ፌ። እግዚአብሔር ያሰበውን አደረገ፥ በቀድሞ ዘመን ያዘዘውን ቃል ፈጸመ፥ አፈረሰ አልራራምም፥ ጠላትንም ደስ አሰኘብሽ፥ የሚያስጨንቁሽንም ቀንድ ከፍ ከፍ አደረገ።


ጌታም ማልዶ ተነሥቶ ባርያዎቹን ነቢያትን ሁሉ ወደ እናንተ ላከ፤ ልኮም ግን እናንተ አላደመጣችሁም፥ ለመስማትም ጆሮአችሁን አላዘነበላችሁም።


እነርሱ ግን ዐመፁ ቅዱስ መንፈሱንም አስመረሩ፤ ስለዚህ ጠላታቸው ሆነ፤ እርሱ ራሱ ተዋጋቸው።


ወደ ሕግህም ትመልሳቸው ዘንድ አስመሰከርህባቸው፥ ነገር ግን ታበዩ፥ ትእዛዝህንም አልሰሙም፥ ሰውም ባደረገው ጊዜ በሕይወት የሚኖርበትን ፍርድህን ተላለፉ፥ ትከሻቸውንም ሰጡ፥ አንገታቸውን አደነደኑ፥ አልሰሙምም።


“ነገር ግን እንቢተኞች ነበሩ፥ ዐመፁብህም፥ ሕግህንም ወደ ኋላቸው ጣሉት፥ ወደ አንተም ይመለሱ ዘንድ የመሰከሩባቸውን ነቢያትህን ገደሉ፥ እጅግም አስቆጡህ።


እርስ በርሳቸውም ባልተስማሙ ጊዜ፥ ጳውሎስ አንዲት ቃል ከተናገረ በኋላ ሄዱ፤ እንዲህም አለ፦ መንፈስ ቅዱስ በነቢዩ በኢሳይያስ ለአባቶቻችን


በበረሃም አርባ ዓመት ያህል መገባቸው።


ጌታም ከእንግዲህ ወዲህ የሥራችሁን ክፋትና ያደረጋችሁትን ርኩሰት መታገሥ አልቻለም፤ ስለዚህ ምድራችሁ ባድማ መሣቀቂያም መረገሚያም ሆናለች ዛሬም እንደሆነ የሚኖርባት የለም።


አባቶቻችሁ ከግብጽ ምድር ከወጡበት ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ፥ በየዕለቱ እየማለድሁ ባርያዎቼን ነቢያትን ሁሉ ደጋግሜ ላክሁባችሁ።


አቤቱ፥ አንተ ግን መሓሪና ርኅሩኅ አምላክ ነህ፥ ለቁጣ የዘገየህ፥ ጽኑ ፍቅርህና እውነትህ የበዛ፥


እንዲያስተምራቸው መልካሟን መንፈስህን ሰጠሃቸው፥ መናህን ከአፋቸው አልከለከልክም፥ ለጥማታቸውም ውኃን ሰጠሃቸው።


አንዳንዶች የሚዘገይ እንደሚመስላቸው፥ ጌታ ስለ ተስፋ ቃሉ አይዘገይም፤ ነገር ግን ሰው ሁሉ ለንስሓ እንዲበቃና ማንም እንዳይጠፋ ወዶ ስለ እናንተ ይታገሣል።


ከእነርሱም ሁለት ሰዎች በሰፈሩ ውስጥ ቀርተው ነበር፥ የአንዱም ስም ኤልዳድ ሲሆን የሁለተኛው ስም ደግሞ ሞዳድ ይባል ነበረ፤ መንፈስም ወረደባቸው፤ እነርሱም ከተጻፉት ጋር ነበሩ ወደ ድንኳኑ ግን ወጥተው አልሄዱም ነበር፤ በሰፈሩም ውስጥ ሳሉ ትንቢት ተናገሩ።


ያችን ትውልድ አርባ ዓመት ተጸየፍኳት፦ ሁልጊዜ ልባቸው ይስታል፥ “እነርሱም መንገዴን አላወቁም” አልሁ።


በትእዛዝ ላይ ትእዛዝ፥ በትእዛዝ ላይ ትእዛዝ፥ በደንብ ላይ ደንብ፥ በደንብ ላይ ደንብ፤ ጥቂት በዚህ ጥቂት በዚያ ነው።


ስለ ስሜ ቁጣዬን አዘገያለሁ፥ እንዳለጠፋህም ስለ ምስጋናዬ እታገሣለሁ።


የሠራዊት ጌታም በቀደሙት ነቢያት እጅ በመንፈሱ የላከውን ሕጉንና ቃሉን እንዳይሰሙ ልባቸውን እንደ አልማዝ አጠነከሩ፤ ስለዚህ ከሠራዊት ጌታ ታላቅ ቁጣ መጣ።


የአሦር ንጉሠ ነገሥት እስራኤላውያንን ማርኮ ወደ አሦር በመውሰድ ከእነርሱ ጥቂቶቹ በሐላሕ ከተማ ጥቂቶቹ በጎዛን አውራጃ በሚገኘው በሐቦር ወንዝ አጠገብ፥ ሌሎቹ ደግሞ በሜዶን ከተሞች እንዲሰፍሩ አደረገ።


እግዚአብሔርም በአገልጋዮቹ በነቢያት አማካይነት እንዲህ ሲል ተናገረ፦


ወደ ጌታም እንዲመልሱአቸው ነቢያትን ይልክላቸው ነበር፤ መሰከሩባቸውም፥ እነርሱ ግን አላደመጡም።


ስለዚህ አምላካችን ሆይ ከዚህ በኋላ ምን እንላለን? ትእዛዛትህን ትተናልና፤


ሆኖም በማለዳ ተነሥቼ ባርያዎቼን ነቢያትን ሁሉ እንዲህ ብዬ ላክሁባችሁ፦ ‘እባካችሁ፥ እንደዚህ ያለ የጠላሁትን ርኩስ ነገር አታድርጉ።’


ነገር ግን አልሰሙም ከክፋታቸውም ተመልሰው ለሌሎች አማልክት ላለማጠን ጆሮአቸውን አላዘነበሉም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች