Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ነህምያ 8:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 በሰባተኛው ወር ባለው በዓል የእስራኤል ልጆች በዳስ እንዲቀመጡ ጌታ በሙሴ በኩል ያዘዘውን በሕጉ ውስጥ ተጽፎ አገኙ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 እስራኤላውያን በሰባተኛው ወር በሚውለው በዓል በዳስ ውስጥ እንዲቀመጡ እግዚአብሔር በሙሴ አማካይነት የሰጠውን ትእዛዝ በሕጉ ውስጥ ተጽፎ አገኙ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 እስራኤላውያን ሕጉን በሚያነቡበት ጊዜ የሰባተኛውን ወር በዓል በዳስ ውስጥ ሆነው እንዲያከብሩ መታዘዙን እግዚአብሔር በሙሴ አማካይነት ባዘዘው ሕግ ውስጥ ተጽፎ አገኙ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ወር ባለው በዓል የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በዳስ ይቀ​መጡ ዘንድ በከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸ​ውና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ይና​ገ​ሩና ያውጁ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሙሴ እጅ እን​ዳ​ዘዘ በሕጉ ውስጥ ተጽፎ አገኙ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14-15 በሰባተኛውም ወር ባለው በዓል የእስራኤል ልጆች በዳስ ይቀመጡ ዘንድ በከተሞቻቸውና በኢየሩሳሌምም፦ ወደ ተራራ ሂዱ፥ የዘይትና የበረሀ ወይራ የባርሰነትም የዘንባባም የለመለመውን ዛፍ ቅርንጫፍ አምጡ፥ እንደ ተጻፈውም ዳሶችን ሥሩ ብለው ይናገሩ ያውጁም ዘንድ እግዚአብሔር በሙሴ እጅ እንዳዘዘ በሕጉ ውስጥ ተጽፎ አገኙ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ነህምያ 8:14
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ያዕቆብ ግን ወደ “ሱኮት” ሄደ፥ ከዚያም ለራሱ ቤትን ሠራ፥ ለከብቶቹም ዳሶችን አደረገ። ስለዚህም የዚያን ቦታ ስም “ሱኮት” ብሎ ጠራው።


እንደተጻፈውም የዳስ በዓል አከበሩ፤ እንደ ሥርዓቱም የዕለቱን የሚቃጠል መሥዋዕት በዕለቱ በቍጥር አቀረቡ፤ የዕለቱን ነገር በዕለቱ።


በሁለተኛው ቀን ከሕዝቡ ሁሉ አለቆች የሆኑ አባቶች፥ ካህናቱ፥ ሌዋውያኑም የሕጉን ቃል እንዲተረጉምላቸው ወደ ጸሐፊው ወደ ዕዝራ ተሰበሰቡ።


“ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ተናገር፦ በዚህ በሰባተኛው ወር ከዐሥራ አምስተኛው ቀን ጀምሮ ሰባት ቀን ለጌታ የዳስ በዓል ነው።


የአይሁድም የዳስ በዓል ቀርቦ ነበር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች