Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ነህምያ 6:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 እኔም እንዲህ ብዬ መልእክተኞችን ላክሁባቸው፦ “ትልቅ ሥራ እሠራለሁ፥ መውረድም አልችልም፤ ሥራውን ትቼ ወደ እናንተ በመውረዴ ሥራው ለምን ይቆማል?”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 እኔም፣ “ታላቅ ሥራ እየሠራሁ ስለ ሆነ፣ ወዳላችሁበት ስፍራ መውረድ አልችልም፤ ትቼው ወደ እናንተ ወርጄ ሥራው ለምን ይቆማል?” በማለት ይህን መልስ የሚያደርሱ መልእክተኞችን ወደ እነርሱ ላክሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 እኔም “አስቸኳይ ሥራ ስላለብኝ ተግባሬን አቁሜ እናንተ ወዳላችሁበት ስፍራ መውረድ አልችልም፤ ወደ እናንተ ለመምጣት ተብሎ ለምን ሥራው ይቆማል?” አልኳቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 እኔም እን​ዲህ ስል መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላክ​ሁ​ባ​ቸው፥ “እኔ ታላቅ ሥራ እሠ​ራ​ለሁ፤ እወ​ር​ድም ዘንድ አይ​ቻ​ለ​ኝም። ስለ​ምን ወደ እና​ንተ በመ​ም​ጣ​ቴና በመ​ው​ረዴ ሥራው ይታ​ጐ​ላል? ሥራ​ውን እንደ ፈጸ​ምሁ እመ​ጣ​ለሁ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 እኔም፦ ትልቅ ሥራ እሠራለሁ፥ እወርድም ዘንድ አይቻለኝም፥ ሥራውን ትቼ ወደ እናንተ በመውረዴ ስለ ምን ሥራው ይታጐላል? ብዬ መልእክተኞችን ላክሁባቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ነህምያ 6:3
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

መኳንንቱን፥ ሹማምቱንና የቀሩትን ሕዝብ እንዲህ አልኋቸው፦ “ሥራው ብዙና ሰፊ ነው፥ እኛም በቅጥሩ ላይ አንዱ ከሌላው ርቆ ተለያይተናል፤


ሰንባላጥና ጌሼም እንዲህ ብለው ላኩብኝ፦ “ናና በኦኖ ሜዳ ባሉት መንደሮች እንገናኝ፤” ነገር ግን ክፉ ሊያደርሱብኝ አቅደው ነበር።


ይህንኑ ቃል አራት ጊዜ ላኩብኝ፤ እኔም ይህንኑ ቃል መለስኩላቸው።


የዋህ ቃልን ሁሉ ያምናል፥ ብልህ ግን አካሄዱን ይመለከታል።


አንተ በምትሄድበት በሲኦል ሥራና አሳብ እውቀትና ጥበብ አይገኙምና እጅህ ለማድረግ የምታገኘውን ሁሉ እንደ ኃይልህ አድርግ።


“እነሆ እንደ በጎች በተኩላዎች መካከል እልካችኋለሁ፤ ስለዚህ እንደ እባብ ብልሆች እንደ ርግብም የዋሆች ሁኑ።


‘ይህ ሰው ሊሠራ ጀምሮ መደምደም አቃተው፤’ ብለው ሊቀልዱበት ይጀምራሉ።


ቀን ሳለ የላከኝን ሥራ ላደርግ ይገባኛል፤ ማንም ሊሠራ የማይችልባት ሌሊት ትመጣለች።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች