ነህምያ 6:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)17 ደግሞም በእነዚያ ቀኖች የይሁዳ መኳንንቶች ብዙ ደብዳቤዎቻቸውን ወደ ጦቢያ ይልኩ ነበር፥ የጦብያም ወደ እነርሱ ይመጡ ነበር። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም17 በዚያ ጊዜ የይሁዳ መኳንንት ለጦቢያ ብዙ ደብዳቤ ይልኩ ነበር፤ ከጦቢያም መልስ ይላክላቸው ነበር። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም17-18 የኢራሕ ልጅ ሴኬን የጦብያ አማች ስለ ነበርና ልጁ ዮሐናንም የቤሬክያን ልጅ የሜሱላንን ሴት ልጅ አግብቶ ስለ ነበረ ከይሁዳ ብዙዎቹ ከእርሱ ጋር ተማምለው ነበር፤ እንዲሁም የይሁዳ ባለ ሥልጣኖች በዚያው ወቅት ከጦብያ ጋር ብዙ የደብዳቤዎች መለዋወጥ ያደርጉ ነበር። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)17 በዚያም ወራት ብዙ የይሁዳ አለቆች ወደ ጦብያ ደብዳቤዎችን ይልኩ ነበር፤ የጦብያም ደብዳቤዎች ወደ እነርሱ ይመጡ ነበር። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)17-18 ጦብያም የኤራ ልጅ የሴኬንያ አማች ስለ ነበረ፥ ልጁም ይሆሐናን የቤራክያን ልጅ የሜሱላምን ሴት ልጅ ስላገባ፥ በይሁዳ ብዙ ሰዎች ከእርሱ ጋር ተማምለው ነበርና በዚያ ወራት ብዙ የይሁዳ አለቆች ወደ ጦብያ ደብዳቤዎች ይልኩ ነበር፥ የጦብያም ደብዳቤዎች ወደ እነርሱ ይመጡ ነበር። ምዕራፉን ተመልከት |