ነህምያ 6:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)14 አምላኬ ሆይ፥ ጦቢያን፥ ሰንባላጥን ስለዚህ ሥራቸው ደግሞም ሊያስፈራሩኝ ነቢያቱን ኖዓድያና የተቀሩት ነቢያትን አስብ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም14 አምላኬ ሆይ፤ ስለ ፈጸሙት ድርጊት ጦቢያንና ሰንባላጥን ዐስብ፤ ሊያስፈራሩኝ የሞከሩትን ነቢያቱን ኖዓድያንና ሌሎቹን ነቢያትም ዐስብ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም14 እኔም “አምላክ ሆይ፥ ጦቢያና ሰንባላጥ ያደረጉትን ሁሉ ተመልከት፤ ፍረድባቸውም፤ ኖዓድያ የተባለችው ሴት ነቢይትና ሌሎቹም ነቢያት እኔን ለማስፈራራት ያደረጉትን ሁሉ አስብ” በማለት ጸለይኩ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)14 አምላኬ ሆይ፥ ስለዚህ ሥራቸው ጦቢያንና ሰንባላጥን፥ ነቢይቱንም ኖዓድያን ያስፈራሩኝ ዘንድ የፈለጉትን፥ የቀሩትንም ነቢያት አስብ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)14 አምላኬ ሆይ፥ ስለዚህ ሥራቸው ጦብያንና ሰንባላጥን ያስፈራሩኝም ዘንድ የወደዱትን ነቢይቱን ኖዓድያን የቀሩትንም ነቢያት አስብ። ምዕራፉን ተመልከት |