ነህምያ 5:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)9 እንዲህም አልኳቸው፦ የምታደርጉት ነገር መልካም አይደለም፤ ጠላቶቻችን አሕዛብ እንዳይሰድቡን አምላካችንን በመፍራት መሄድ አይገባችሁምን? ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም9 ስለዚህ በመቀጠል እንዲህ አልሁ፤ “ይህ የምታደርጉት ነገር ትክክል አይደለም፤ የጠላቶቻችንን የአሕዛብን ስድብ ለማስወገድ የአምላካችንን መንገድ በፍርሀት መከተል አይገባችሁምን? ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም9 እኔ ግን ንግግሬን በመቀጠል እንዲህ አልኳቸው፤ “ያደረጋችኹት ነገር ትክክል አይደለም! እግዚአብሔርን መፍራትና ትክክል የሆነውን ነገር ማድረግ በተገባችሁ ነበር፤ ይህን አድርጋችሁ ቢሆን ኖሮ፥ አሕዛብ ጠላቶቻችን ባልተዘባበቱብንም ነበር። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)9 ደግሞም አልሁ፥ “የምታደርጉት ነገር መልካም አይደለም፤ ጠላቶቻችን አሕዛብ እንዳይሰድቡን አምላካችንን በመፍራት ትሄዱ ዘንድ አይገባችሁምን? ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)9 ደግሞም አልሁ፦ የምታደርጉት ነገር መልካም አይደለም፥ ጠላቶቻችን አሕዛብ እንዳይሰድቡን አምላካችንን በመፍራት ትሄዱ ዘንድ አይገባችሁምን? ምዕራፉን ተመልከት |