Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ነህምያ 5:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 በይሁዳ ምድር ላይ ገዢ እንድሆን ከተሾምሁበት፥ ከንጉሡ አርታሕሻስት ከሀያኛው ዓመት ጀምሮ እስከ ሠላሳ ሁለተኛው ዓመት ድረስ ለዐሥራ ሁለት ዓመት ያህል እኔና ወንድሞቼ የንጉሡን ምግብ አልበላንም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ከዚህም በላይ በይሁዳ ምድር አገረ ገዥ ሆኜ ከተሾምሁበት፣ ከአርጤክስስ ሃያኛ ዓመት ጀምሮ እስከ ሠላሳ ሁለተኛው ዘመነ መንግሥቱ ድረስ፣ ለዐሥራ ሁለት ዓመት እኔም ሆንሁ ወንድሞቼ ለአንድ አገረ ገዥ የተመደበውን ምግብ ተቀብለን አልበላንም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 አርጤክስስ ንጉሠ ነገሥት ከሆነበት ከኻኛው ዓመት ጀምሮ ሠላሳ ሁለት ዓመት እስከ ሆነው ድረስ እኔ የይሁዳ ገዢ በሆንኩበት የዐሥራ ሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ዘመዶቼም ሆኑ ወይም እኔ ራሴ ለአንድ አገረ ገዢ የሚገባውን ምግብ አልበላንም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ንጉ​ሡም በይ​ሁዳ ምድር ላይ አለቃ እሆን ዘንድ ካዘ​ዘኝ ጊዜ ጀምሮ ከን​ጉሡ ከአ​ር​ተ​ሰ​ስታ ከሃ​ያ​ኛው ዓመት እስከ ሠላሳ ሁለ​ተ​ኛው ዓመት ድረስ ዐሥራ ሁለት ዓመት ያህል እኔና ወን​ድ​ሞች ለአ​ለቃ የሚ​ገ​ባ​ውን ቀለብ አል​በ​ላ​ንም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ንጉሡም በይሁዳ ምድር ላይ አለቃ እሆን ዘንድ ካዘዘኝ ጊዜ ጀምሮ ከንጉሡ ከአርጤክስስ ከሀያኛው ዓመት እስከ ሠላሳ ሁለተኛው ዓመት ድረስ አሥራ ሁለት ዓመት ያህል እኔና ወንድሞቼ ለአለቃ የሚገባውን ስንቅ አልበላንም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ነህምያ 5:14
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የሐካልያ ልጅ የነህምያ ቃል። በሃያኛው ዓመት በኪስሌው ወር በሱሳ ግንብ ሳለሁ፥ እንዲህ ሆነ፤


በዚህ ጊዜ በኢየሩሳሌም አልነበርሁም፤ በባቢሎን ንጉሥ በአርታሕሻስት በሠላሳ ሁለተኛው ዓመት ወደ ንጉሡ ሄጄ ነበርና፤ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ከንጉሡ ፈቃድ ጠየቅሁ፤


እንዲህም ሆነ በንጉሡ አርታሕሻስት በሀያኛው ዓመት በኒሳን ወር፥ የወይን ጠጅ በፊቱ ነበረ፥ የወይን ጠጁን አንሥቼ ለንጉሡ ሰጠሁት። ከዚህ ቀደም በፊቱ አዝኜ አላውቅም።


አምስት መክሊት የተቀበለውም ሄዶ ነገደበትና ሌላ አምስት አተረፈ፤


እንግዲህ ዋጋዬ ምንድነው? በወንጌል ካለኝ መብት በሙሉ ሳልጠቀምበት ወንጌልን እየሰበክሁ ወንጌልን ያለ ክፍያ ባስተምር ነው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች