ነህምያ 4:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)6 በአጠገባቸው የተቀመጡ አይሁድ መጥተው፦ “ከስፍራው ሁሉ ይመጡብናል” ብለው ዐሥር ጊዜ ነገሩን። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም6 ሕዝቡ ከልቡ ስለሚሠራ፣ ቅጥሩን እኩሌታው ድረስ መልሰን ሠራነው። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም6 እኛም ቅጽሩን መልሶ የማነጹን ሥራ ቀጠልን፤ ሕዝቡ በትጋት በመሥራቱ ሥራው እየተፋጠነ ሄዶ ግማሽ ደረሰ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)6 ቅጥሩንም ሠራን፤ ቅጥሩም ሁሉ እስከ እኩሌታው ድረስ ተጋጠመ፤ ሕዝቡ ከልብ ይሠራ ነበርና። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)6 ቅጥሩንም ሠራን፥ ቅጥሩም ሁሉ እስከ እኩሌታው ድረስ ተጋጠመ፥ የሕዝቡም ልብ ለሥራው ጨከነ። ምዕራፉን ተመልከት |