ነህምያ 4:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)17 እኔ፥ ወንድሞቼ፥ ጎበዛዝቶቼና ከኋላዬ የነበሩት ጠባቂዎች ልብሳችንን አናወልቅም ነበር። ወደ ውኃም ስንሄድ እያንዳንዱ መሣሪያውን ይዞ ይሄድ ነበር። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም17 እነርሱም ቅጥሩን ይገነቡ ነበር፤ ዕቃ የሚሸከሙት በአንድ እጃቸው ሥራቸውን ሲሠሩ፣ በሌላው እጃቸው የጦር መሣሪያቸውን ይዘው ነበር፤ ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም17 ቅጽሩን የሚሠሩትን ሁሉ ያበረታቱ ነበር፤ ሌላው ቀርቶ፥ ተሸካሚዎቹ ጭምር በአንድ እጃቸው ሲሠሩ፥ በሌላ እጃቸው የጦር መሣሪያ ይዘው ለመከላከል ዝግጁዎች ነበሩ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)17 ቅጥሩንም የሚሠሩትና ሸክም ተሸካሚዎቹ በአንድ እጃቸው ይሠሩ ነበር፤ በአንድ እጃቸውም የጦር መሣሪያቸውን ይይዙ ነበር። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)17 ቅጥሩንም የሚሠሩትና ተሸካሚዎቹ በአንድ እጃቸው ይሠሩ ነበር፥ በአንድ እጃቸውም የጦር መሣሪያቸውን ይይዙ ነበር። ምዕራፉን ተመልከት |