Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ነህምያ 4:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 እኛ ሥራውን ሠራን፤ እኩሌቶቹ ደግሞ ጎሕ ሲቀድ ጀምሮ ከዋክብት እስኪወጡ ድረስ ጦር ይይዙ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 አድማቸውን እንዳወቅንባቸውና እግዚአብሔርም ዕቅዳቸውን ከንቱ እንዳደረገባቸው ጠላቶቻችን በሰሙ ጊዜ፣ ሁላችን ወደ ቅጥሩ፣ እያንዳንዳችንም ወደየሥራችን ተመለስን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ጠላቶቻችንም የተማማሉበትን አድማ የደረስንበት መሆኑን ሰሙ፤ እግዚአብሔርም ዕቅዳቸውን እንዳከሸፈባቸው ተገነዘቡ፤ ከዚያ በኋላ ሁላችንም የቅጽሩን ግንብ መሥራታችንን ቀጠልን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ጠላ​ቶ​ቻ​ች​ንም እንደ ዐወ​ቅ​ን​ባ​ቸው፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ምክ​ራ​ቸ​ውን ከንቱ እን​ዳ​ደ​ረ​ገው ሰሙ፤ እኛም ሁላ​ችን ወደ ቅጥሩ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ችን ወደ ሥራ​ችን ተመ​ለ​ስን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ጠላቶቻችንም ይህ ነገር እንደ ደረሰልን፥ እግዚአብሔርም ምክራቸውን ከንቱ እንዳደረገው ሰሙ፥ እኛም ሁላችን ወደ ቅጥሩ እያንዳንዳችን ወደ ሥራችን ተመለስን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ነህምያ 4:15
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በዚህ ጊዜ፥ “ከአቤሴሎም ጋር ካሤሩት መካከል አንዱ አኪጦፌል ነው” ብለው ለዳዊት ነገሩት። ዳዊትም፥ “ጌታ ሆይ! እባክህን የአኪጦፌልን ምክር ወደ ከንቱነት ለውጠው” ሲል ጸለየ።


አቤሴሎምና የእስራኤል ሰዎች ሁሉም “ከአኪጦፌል ምክር ይልቅ የአርካዊው የሑሻይ ምክር ይሻላል” አሉ፤ ጌታ በአቤሴሎም ላይ ጥፋት ለማምጣት፥ ጌታ መልካም የነበረው የአኪጦፌል ምክር ተቀባይነት እንዲያጣ አድርጎአል።


እንዲሁም ደግሞ በዚያ ጊዜ ሕዝቡን፦ “በሌሊት ጠባቂዎች፥ በቀንም ሥራ እንዲሰሩልን እያንዳንዱ ከአገልጋዩ ጋር በኢየሩሳሌም ውስጥ ይደር፤” አልኋቸው።


ያለ ጌታ የሚሠምር፥ ጥበብም የለም፥ ማስተዋልም የለም፥ ምክርም የለም።


የሐሰተኞችን ምልክት ከንቱ አደርጋለሁ፥ ምዋርተኞችንም አሳብዳለሁ፥ ጥበበኞቹንም ወደ ኋላ እመልሳለሁ፥ እውቀታቸውንም ስንፍና አደርጋለሁ፤


ተመካከሩ፤ ግን አይሳካም፤ ዕቅድ አውጡ፤ ሆኖም አይጸናም፤ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነውና።


ይህም ቤቱን ለአገልጋዮቹ ትቶ፥ እያንዳንዱን አገልጋይ በየሥራ ድርሻው ላይ አሰማርቶ፥ በረኛው ነቅቶ እንዲጠብቅ አዝዞ የሄደውን ሰው ይመስላል።


ለሥራ ከመትጋት አትለግሙ፤ በመንፈስ የምትቃጠሉ ሁኑ፤ ጌታን አገልግሉ፤


በጸጥታ ለመኖር እንድትተጉ፥ በራሳችሁም ጉዳይ ላይ እንድታተኩሩ፥ እንዳዘዝናችሁም በራሳችሁ እጅ እንድትሰሩ እንለምናችኋለን፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች