ነህምያ 3:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)5 በአጠገባቸውም ቴቁአውያን አደሱ፤ መኳንንቶቻቸው ግን ለጌታቸው ሥራ አንገታቸውን አልሰጡም። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም5 የሚቀጥለውን ክፍል የቴቁሔ ሰዎች መልሰው ሠሩ፤ መኳንንታቸው ግን በተቈጣጣሪ አሠሪዎቻቸው ሥር ሆነው በሥራው መጠመድ አልፈለጉም። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም5 የተቆዓ ከተማ ሰዎች ከዚያ ቀጥሎ ያለውን ክፍል ሠሩ፤ ነገር ግን የከተማይቱ ሹማምንት በተቈጣጣሪዎች የተመደበላቸውን የጒልበት ሥራ መሥራትን እምቢ አሉ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)5 በአጠገባቸውም ቴቁሓውያን ይሠሩ ጀመሩ፤ ታላላቆቻቸው ግን ለሥራው አንገታቸውን አላዋረዱም። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)5 በአጠገባቸውም ቴቁሐውያን አደሱ፥ ታላላቆቻቸው ግን ለጌታቸው ሥራ አንገታቸውን አላዋረዱም። ምዕራፉን ተመልከት |