Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ነህምያ 3:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 የስናአ ልጆች “የዓሣ በር” ሠሩ፤ ሰረገሎቹን አኖሩ፥ በሮቹን አቆሙ፥ ቁልፎቹንና መወርወሪያዎቹንም ሠሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 የዓሣ በሩን የሃስናአ ልጆች ሠሩ፤ እነርሱም ምሰሶዎቹን አቁመው መዝጊያዎቹን፣ መቀርቀሪያዎቹንና መወርወሪያዎቹን በየቦታቸው አኖሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 የሃስናአ ጐሣ አባሎች የዓሣ ቅጽር በር የተባለውን ሠሩ፤ ምሰሶዎችንም አቆሙለት፤ በሮችንም ገጠሙ፤ ለበሮቹም መዝጊያ፥ መወርወሪያና ቊልፎችን አበጁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 የአ​ስ​ናሃ ልጆ​ችም የዓሣ በር ሠሩ፤ ሠረ​ገ​ሎ​ቹ​ንም አኖሩ፤ ሳን​ቃ​ዎ​ቹ​ንም አቆሙ፥ ቍል​ፎ​ቹ​ንና መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎ​ቹ​ንም አደ​ረጉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 የሃስናአ ልጆችም የዓሣ በር ሠሩ፥ ሰረገሎቹን አኖሩ፥ ሳንቃዎቹንም አቆሙ፥ ቁልፎቹንና መወርወሪያዎቹንም አደረጉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ነህምያ 3:3
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከ “ኤፍሬም በር” በላይ፥ ከ “አሮጌው በር” በላይ፥ በ “ዓሣ በር” በ “ሐናንኤል ግንብ”፥ በሃሜአ ግንብ እስከ በጎች በር ድረስ ሄዱ፥ በዘበኞችም በር አጠገብ ቆሙ።


ከዚህ በኋላ በዳዊት ከተማ በስተ ውጭው ከግዮን ምዕራብ በሸለቆው ውስጥ እስከ ዓሳ በር መግቢያ ድረስ ቅጥር ሠራ። በዖፌልም አዞረበት፥ እጅግም ከፍ አደረገው፤ በተመሸጉትም በይሁዳ ከተሞች ሁሉ የጭፍራ አለቆችን አኖረ።


በዚያ ቀን ይላል ጌታ፥ “የዓሣ በር” የጩኸት ድምፅ፥ ከከተማውም በሁለተኛው ክፍል ዋይታ፥ ከኮረብቶቹም ታላቅ ሽብር ይሆናል።


ለንጉሡ ደን ጠባቂ ለአሳፍ በቤቱ አጠገብ ላለው ምሽግ በሮች፥ ለከተማው ቅጥር፥ ለምገባበትም ቤት እንጨት እንዲሰጠኝ ደብዳቤ ይሰጠኝ” አልኩት። ንጉሡም በእኔ ላይ እንዳለችው እንደ አምላኬ መልካም እጅ ሰጠኝ።


እንዲህም ሆነ ቅጥሩ ከተሠራ በኋላ፥ በሮቹን ካቆምሁ በኋላ፥ በር ጠባቂዎች፥ መዘምራንና ሌዋውያን ተሾሙ፤


እንዲህም ሆነ ምንም እንኳ እስከዚያ ጊዜ ድረስ በበሮቹ ውስጥ ሳንቃዎቹን ባልገጥምም ቅጥሩን እንደሠራሁ፥ አንድም የፈረሰ እንዳልቀረ ሰንባላጥ፥ ጦቢያና ዓረባዊው ጌሼም የቀሩትም ጠላቶቻችን በሰሙ ጊዜ፥


የፋሴሐ ልጅ ዮያዳ የቤሶዴያ ልጅ ሜሹላም “አሮጌ በር” አደሱ፤ ሰረገሎቹን አኖሩ፥ በሮቹንም አቆሙ፥ ቁልፎቹንና መወርወሪያዎቹንም አደረጉ።


በአጠገባቸውም የቆጽ ልጅ የኡሪያ ልጅ ሜሬሞት አደሰ። በአጠገባቸውም የመሼዛቤል ልጅ የቤሬክያ ልጅ ሜሹላም አደሰ። በአጠገባቸውም የባዓና ልጅ ጻዶቅ አደሰ።


የደጆችሽን መወርወሪያ አጽንቶአልና፥ ልጆችንም በውስጥሽ ባርኮአልና።


የስናአ ልጆች፥ ሦስት ሺህ ስድስት መቶ ሠላሳ።


የሰናአ ልጆች፥ ሦስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሠላሳ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች