ነህምያ 3:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)25 የኡዛይ ልጅ ፓላል በግንቡ መደገፊያ ፊት ለፊት ያለውንና በዘበኞች አደባባይ አጠገብ ከላይኛው የንጉሡ ቤት ወጥቶ የቆመውን ግንብ ሠራ፥ ከእርሱም በኋላ የፋኖስ ልጅ ፈዳያ ሠራ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም25 የኡዛይ ልጅ ፋላል ከቅጥሩ ማእዘን ትይዩና በዘብ መጠበቂያው አደባባይ አጠገብ ካለው ከላይኛው ቤተ መንግሥት መጠበቂያ ግንብ ጀምሮ ያለውን መልሶ ሠራ። ከርሱም ቀጥሎ የፋሮስ ልጅ ፈዳያና ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም25-26 የዑዛይ ልጅ ፓላል ከቅጽሩ ማእዘንና በዘብ መጠበቂያው አደባባይ አጠገብ ከሚገኘው ከላይኛው ቤተ መንግሥት መጠበቂያ ግንብ ጀምሮ ያለውን ክፍል ሁሉ ሠራ። የፓርዖሽ ልጅ ፐዳያ ደግሞ በውሃው ቅጽር በር አጠገብ ወደምሥራቅ የሚያመለክተውን ስፍራና የቤተ መቅደሱን መጠበቂያ ግንብ ይኸውም የቤተ መቅደሱ ሠራተኞች በሚኖሩበት የከተማይቱ አንድ ክፍል በሆነው “ዖፌል” ተብሎ በሚጠራው ስፍራ አጠገብ ያለውን ክፍል ሠራ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)25 የኡዛይ ልጅ ፋልል በማዕዘኑ አንጻር ያለውንና በዘበኞች አደባባይ አጠገብ ከላይኛው የንጉሡ ቤት ወጥቶ የቆመውን ግንብ ሠራ። ከእርሱም በኋላ የፋሮስ ልጅ ፈዳያ ሠራ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)25 የኡዛይ ልጅ ፋላል በማዕዘኑ አንጻር ያለውንና በዘበኞች አደባባይ አጠገብ ከላይኛው የንጉሡ ቤት ወጥቶ የቆመውን ግንብ ሠራ፥ ከእርሱም በኋላ የፋኖስ ልጅ ፈዳያ ሠራ። ምዕራፉን ተመልከት |