Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ነህምያ 3:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 በአጠገቡ የሚጽጳ ገዢ የኢያሱ ልጅ ዔዜር በግንቡ መደገፊያ ወደ ጦር መሣሪያ ግምጃ ቤት መወጣጫ ፊት ለፊት ያለውን ሁለተኛውን ክፍል አደሰ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ከርሱም ቀጥሎ ወደ ጦር መሣሪያ ግምጃ ቤት በሚያወጣውና እስከ ማእዘኑ በሚደርሰው ትይዩ ያለውን ሌላ ክፍል የምጽጳ ገዥ የኢያሱ ልጅ ኤጽር መልሶ ሠራ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 የምጽጳ ወረዳ ገዥ የሆነው የኢያሱ ልጅ ዔዜር በጦር መሣሪያው ግምጃ ቤት ፊት ለፊት ያለውን እስከ ቅጽሩ መመለሻ ማእዘን ድረስ ያለውን ሁሉ ሠራ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 በአ​ጠ​ገ​ቡም የመ​ሴፋ ገዢ የኢ​ያሱ ልጅ አዙር በማ​ዕ​ዘኑ አጠ​ገብ በመ​ወ​ጣ​ጫው ግንብ አን​ጻር ያለ​ውን ሌላ​ውን ክፍል ሠራ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 በአጠገቡም የምጽጳ አለቃ የኢያሱ ልጅ ኤጽር በማዕዘኑ አጠገብ በጦር መሣሪያ ቤት አንጻር ሌላውን ክፍል አደሰ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ነህምያ 3:19
6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዖዝያንም በኢየሩሳሌም በማዕዘኑ በርና በሸለቆው በር ቅጥሩም በዞረበት ማዕዘን አጠገብ ግንቦችን ሠርቶ መሸጋቸው።


ማዓዝያ፥ ቢልጋይ፥ ሽማዕያ፤ እነዚህ ካህናት ነበሩ።


ሌዋውያኑም፦ ኢያሱ፥ ቢኒዊ፥ ቃድሚኤል፥ ሼሬብያ፥ ይሁዳና ከወንድሞቹ ጋር በመሆን የምስጋና መዝሙር ኃላፊ የነበረው ማታንያ።


የሚጽጳም አውራጃ ገዢ የኮልሖዜ ልጅ ሻሉን “የምንጭ በር” አደሰ፤ መልሶ ሠራው፥ ከደነውም፥ በሮቹን አቆመ፥ ቁልፎቹንና መወርወሪያዎቹንም አበጀ፤ በንጉሡ አትክልት ቦታ አጠገብ ያለውን የሼላሕን መዋኛ ቅጥር ከዳዊት ከተማ ወደ ታች እስከሚወርደው ደረጃ ድረስ ሠራ።


ከእርሱም በኋላ ወንድሞቻቸው፥ የቅዒላ አውራጃ እኩሌታ ገዚ የሆነው የሔናዳድ ልጅ ባዋይ አደሱ።


ከእርሱም በኋላ የሔናዳድ ልጅ ቢኑይ ከዓዛርያ ቤት ጀምሮ እስከ የግንቡ መደገፊያ ድረስ ሌላውን ክፍል አደሰ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች