Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ነህምያ 3:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ሐኑንና የዛኖሐ ሰዎችም “የሸለቆ በር” አደሱ፤ መልሰው ሠሩት፥ ሳንቃዎቹንም አቆሙ፥ ቁልፎቹንና መወርወሪያዎቹንም አበጁ፤ ደግሞም እስከ “የፍግ በር” ድረስ አንድ ሺህ ክንድ የሚሆን ቅጥር ሠሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 “የሸለቆ በር” ተብሎ የሚጠራውን የሐኖንና የዛኖ ነዋሪዎች ዐደሱት፤ መልሰው ሠሩት፤ ከሠሩትም በኋላ መዝጊያዎቹን በየቦታቸው አኖሩ፤ መወርወሪያዎቹንና መቀርቀሪያዎቹንም አበጁ። እንዲሁም የቈሻሻ መጣያ በር ተብሎ እስከሚጠራው ድረስ ያለውን አንድ ሺሕ ክንድ ቅጥር መልሰው ሠሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ሐኑንና የዛኖሐ ነዋሪዎች ተባብረው የሸለቆውን ቅጽር በር በማደስ ሠሩ፤ ለቅጽር በሩም መዝጊያዎችን አቁመው ቊልፎችንና መወርወሪያዎችን አበጁለት፤ እስከ ጒድፍ መጣያ ቅጽር በር 440 ሜትር ርዝመት ያለውንም ቅጽር እንደገና ሠሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ሐኖ​ንና የዘ​ናን ሰዎ​ችም የሸ​ለ​ቆ​ውን በር አደሱ፤ ሠሩት፤ ሳን​ቃ​ዎ​ቹ​ንም አቆሙ፥ ቍል​ፎ​ቹ​ንና መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎ​ቹ​ንም አደ​ረጉ፤ ደግ​ሞም እስከ ጕድፍ መጣያ በር ድረስ አንድ ሺህ ክንድ የሚ​ሆን ቅጥር ሠሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ሐኖንና የዛኖዋ ሰዎችም የሸለቆውን በር አደሱ፥ ሠሩት፥ ሳንቃዎቹንም አቆሙ፥ ቁልፎቹንና መወርወሪያዎቹንም አደረጉ፥ ደግሞም እስከ ጉድፍ መጣያው በር ድረስ አንድ ሺህ ክንድ የሚሆን ቅጥር ሠሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ነህምያ 3:13
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አይሁዳዊቱም ሚስቱ የጌዶርን አባት ዬሬድን፥ የሦኮንም አባት ሔቤርን፥ የዛኖዋንም አባት ይቁቲኤልን ወለደች። እነዚህም ሜሬድ ያገባት የፈርዖን ልጅ የቢትያ ልጆች ናቸው።


ዖዝያንም በኢየሩሳሌም በማዕዘኑ በርና በሸለቆው በር ቅጥሩም በዞረበት ማዕዘን አጠገብ ግንቦችን ሠርቶ መሸጋቸው።


ዛኖሓ፥ ዓዱላምና በመንደሮቻቸው፥ ላኪሽና ሜዳዎችዋ፥ ዓዚቃና በመንደሮችዋ፤ እንዲሁ ከቤርሳቤህ ጀምሮ እስከ ሄኖም ሸለቆ ድረስ ሰፈሩ።


በሌሊትም በሸለቆው በር ወጣሁ፥ ወደ “የዘንዶ ምንጭ” እና ወደ “የፍግ በር” ሄድኩ፤ የፈረሰውን የኢየሩሳሌምን ቅጥርና በእሳት የተቃጠሉትን በሮችዋን ተመለከትኩ።


በሌሊት በፈፋው በኩል ወጥቼ ቅጥሩን ተመለከትኩ፤ ተመልሼም በሸለቆው በር ገባሁ፥ ከዚያም ተመለስኩ።


ዛኖዋ፥ ዓይንገኒም፥ ታጱዋ፥ ዓይናም፥


ኢይዝራኤል፥ ዮቅድዓም፥ ዛኖዋሕ፥


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች