Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ነህምያ 3:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 የሐሪም ልጅ ማልኪያና የፓሐት ሞዓብ ልጅ ሐሹብ ሌላውን ክፍልና “የእቶን ግንብ” አደሱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 የካሪም ልጅ መልክያና የፈሐት ሞዓብ ልጅ አሱብ ሌላውን ክፍልና የእቶን ግንብ ተብሎ የሚጠራውን መልሰው ሠሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 የሓሪም ልጅ ማልኪያና የፓሐትሞአብ ልጅ ሐሹብ ከዚያ ቀጥሎ ያለውን ክፍልና “የእቶን ግንብ” ተብሎ የሚጠራውን ግንብ ሠሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 የካ​ሪም ልጅ መል​ክያ፥ የፈ​ሐት ሞዓብ ልጅም አሱብ ሌላ​ውን ክፍ​ልና የእ​ቶ​ኑን ግንብ ሠሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 የካሪም ልጅ መልክያ፥ የፈሐት ሞዓብ ልጅም አሱብ ሌላውን ክፍልና የእቶኑን ግንብ አደሱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ነህምያ 3:11
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከፊት ይሄድ የነበረው ሁለተኛው የምስጋና መዘምራን ክፍል ነበር፤ እኔና የሕዝቡ እኩሌታ በስተ ኋላቸው ነበርን፤ በቅጥሩም ላይ፥ ከ “የእቶኑ ግንብ” በላይ እስከ “ሰፊው ቅጥር” ድረስ፥


የፓሐት ሞዓብ ልጆች የኢያሱ ዮአብ ልጆች፥ ሁለት ሺህ ስምንት መቶ ዐሥራ ሁለት።


ሆዲያ፥ ባኒ፥ ብኒኑ።


ሐጡሽ፥ ሽባንያ፥ ማሉክ፥


ከኢያሱና ከዮአብ ልጆች የሆኑ የፓሐት ሞዓብ ልጆች፥ ሁለት ሺህ ስምንት መቶ ዐሥራ ስምንት።


ከፓሐት ሞዓብ ልጆች የዝራሕያ ልጅ ኤልይሆዔናይ፥ ከእርሱም ጋር ሁለት መቶ ወንዶች፤


ከሓሪም ልጆችም፦ ኤሊዔዜር፥ ዪሺያ፥ ማልኪያ፥ ሽማዕያ፥ ስምዖን፥


በአጠገባቸውም የሐሩማፍ ልጅ ዬዳያ ከቤቱ ፊት ለፊት ያለውን አደሰ። በአጠገቡም የሐሻቤኔያ ልጅ ሐጡሽ አደሰ።


አቤቱ፥ ስለ ፍርድህ የጽዮን ተራራ ደስ ይበለው፥ የይሁዳም ሴት ልጆች ሐሤት ያድርጉ።


የሐሪም ልጆች፥ ሦስት መቶ ሀያ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች