Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ነህምያ 2:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ሖሮናዊው ሳንባላጥና አገልጋይ የሆነው አሞናዊው ጦብያ ለእስራኤል ልጆች መልካምን ነገር የሚሻ ሰው እንደመጣ በሰሙ ጊዜ እጅግ ተበሳጩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ሖሮናዊው ሰንባላጥና አሞናዊው ሹም ጦቢያ ይህን በሰሙ ጊዜ፣ ስለ እስራኤላውያን ደኅንነት የሚቈረቈር ሰው በመምጣቱ እጅግ ተበሳጩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ነገር ግን የቤትሖሮን ከተማ ነዋሪ የሆነው ሰንባላጥና የዐሞን ክፍለ ሀገር ባለሥልጣን የሆነው ጦቢያ ለእስራኤል ሕዝብ ደኅንነት መልካም ነገር የሚሠራ ሰው መምጣቱን ሰምተው እጅግ ተቈጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ሖሮ​ና​ዊ​ውም ሰን​ባ​ላ​ጥና አገ​ል​ጋዩ አሞ​ና​ዊው ጦብያ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መል​ካ​ምን ነገር የሚሻ ሰው እንደ መጣ በሰሙ ጊዜ እጅግ ተበ​ሳጩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ሖሮናዊውም ሰንባላጥና ባሪያው አሞናዊ ጦብያ ለእስራኤል ልጆች መልካምን ነገር የሚሻ ሰው እንደ መጣ በሰሙ ጊዜ እጅግ ተበሳጩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ነህምያ 2:10
26 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እኔም ከቅጥሩ በስተ ኋላ በኩል ባለው በታችኛው ስፍራ ሰይፋቸውን፥ ጦራቸውንና ቀስታቸውን አስይዤ ሕዝቡን በየወገናቸው አቆምኳቸው።


ሖሮናዊው ሳንባላጥ፥ አገልጋይ የሆነው አሞናዊው ጦብያና ዓረባዊው ጌሻም ይህንን ሰሙ፤ አፌዙብን፤ አንቋሸሹንም፤ “ይህ የምታደርጉት ነገር ምንድነው? በንጉሡ ላይ እያመፃችሁ ነውን?” አሉ።


ቁጣ ጭካኔን ያስከትላል፥ ንዴትም እንደ ጎርፍ ነው፥ በቅንዓት ፊት ግን ማን መቆም ይችላል?


ከዚህ ቀደም በአምላካችን ቤት ጓዳዎች ላይ ተሾሞ የነበረው ካህኑ ኤልያሺብ ከጦቢያ ጋር ተወዳጅቶ፥


እንዲህም ሆነ ምንም እንኳ እስከዚያ ጊዜ ድረስ በበሮቹ ውስጥ ሳንቃዎቹን ባልገጥምም ቅጥሩን እንደሠራሁ፥ አንድም የፈረሰ እንዳልቀረ ሰንባላጥ፥ ጦቢያና ዓረባዊው ጌሼም የቀሩትም ጠላቶቻችን በሰሙ ጊዜ፥


የመቅደስ አዛዥና የካህናት አለቆችም ይህን ነገር በሰሙ ጊዜ “እንጃ ይህ ምን ይሆን?” እያሉ ስለ እነርሱ አመነቱ።


ሕዝቡን ስለ አስተማሩና በኢየሱስ የሙታንን ትንሣኤ ስለ ሰበኩ እጅግም ተቆጥተው ወደ እነርሱ ቀረቡ፤


ከሐሴቦን ጮኹ እስከ ኤልያሊና እስከ ያሀጽ ድረስ ድምፃቸውን አሰሙ፤ ከዞዓር እስከ ሖሮናይምና እስከ ዔግላት ሺሊሺያ ድረስ ደርሶአል፤ የኔምሬም ውኃ ደግሞ ይደርቃል።


በሉሒት አቀበት መራር ልቅሶ እያለቀሱ ይወጣሉና፥ በሖሮናይምም ቁልቁለት የጥፋትንና የጣርን ጩኸት ሰምተዋል።


ልቤ ስለ ሞዓብ አለቀሰ፤ ከእርሷ የሚሸሹ ወደ ዞዐር ወደ ዔግላት ሺሊሺያ ኮበለሉ፤ በሉሒት አቀበት ላይ እያለቀሱ ወጡ፤ በሖሮናይምም መንገድ የዋይታ ጩኽት አሰሙ።


ባርያዎች በፈረስ ላይ ሲቀመጡ መሳፍንትም እንደ ባርያዎች በምድር ላይ ሲሄዱ አየሁ።


አገልጋይ በነገሠ ጊዜ፥ ሞኝ እንጀራ በጠገበ ጊዜ፥


ክፉ ሰውም አይቶት ይቈጣል፥ ጥርሱንም ያፋጫል፥ ይቀልጣልም፥ የክፉዎች ምኞት ትጠፋለች።


በዚያም ቀን የሙሴን መጽሐፍ በሕዝቡ ጆሮ ከፍ ባለ ድምፅ አነበቡ፤ አሞናዊ ወይም ሞዓባዊ ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ ለዘለዓለም እንዳይገባ የሚል በዚያ ተጽፎ ተገኘ።


እንዲህም ሆነ፦ ጠላቶቻችን ሁሉ ይህን በሰሙ ጊዜ በዙሪያችን የነበሩ አሕዛብ ሁሉ ፈሩ፥ ዓይናቸውም እያየ ብዙ ውድቀት ሆነ፥ ይህ ሥራ በአምላካችን እንደ ተከናወነ አወቁ።


ከዋነኛውም ካህን ከኤልያሴብ ልጅ ከዮአዳ ልጆች አንዱ ለሖሮናዊው ለሰንበላጥ አማች ነበረ፥ ከእኔም ዘንድ አባረርሁት።


እስማኤልም በምጽጳ የነበረውን የሕዝቡን ትሩፍ ሁሉ፥ የንጉሡን ሴቶች ልጆች የዘበኞቹም አለቃ ናቡዘረዳን ለአኪቃም ልጅ ለጎዶልያስ የሰጠውን በምጽጳ የቀሩትን ሕዝብ ሁሉ ማረከ፤ የናታንያም ልጅ እስማኤል ማርኮ ወደ አሞን ልጆች ለመሄድ ተነሣ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች