Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ነህምያ 13:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 አባቶቻችሁ እንደዚህ አድርገው አልነበረምን? አምላካችንስ ይህን ክፉ ነገር ሁሉ በእኛና በዚህ ከተማ ላይ አምጥቶ አልነበረምን? እናንተም ሰንበትን በማርከሳችሁ በእስራኤል ላይ መዓትን ትጨምራላችሁ አልኋቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 የቀድሞ አባቶቻችሁ ያደረጉት ይህንኑ አልነበረምን? አምላካችንስ ይህን ሁሉ ጥፋት በእኛና በዚች ከተማ ላይ ያመጣው በዚሁ በደላችን አይደለምን? አሁንም እናንተ ሰንበትን በማርከስ የባሰ መከራ በእስራኤል ላይ ታመጣላችሁ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 አምላካችን በእኛና በከተማይቱ ላይ ይህን ጥፋት ያመጣው የቀድሞ አባቶቻችሁ ይህን ጥፋት ስላደረጉ አይደለምን? አሁንም እናንተ ሰንበትን ባለማክበራችሁ የእግዚአብሔርን ቊጣ በእስራኤል ላይ ታነሣሣላችሁ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 አባ​ቶ​ቻ​ችሁ እን​ደ​ዚህ አድ​ር​ገው አል​ነ​በ​ረ​ምን? አም​ላ​ካ​ች​ንስ ይህን ክፉ ነገር ሁሉ በእ​ኛና በዚች ከተማ ላይ አም​ጥቶ አል​ነ​በ​ረ​ምን? እና​ን​ተስ ሰን​በ​ትን በማ​ር​ከ​ሳ​ችሁ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ መዓ​ትን ትጨ​ም​ራ​ላ​ችሁ?”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 አባቶቻችሁ እንደዚህ አድርገው አልነበረምን? አምላካችንስ ይህን ክፉ ነገር ሁሉ በእኛና በዚህ ከተማ ላይ አምጥቶ አልነበረምን? እናንተም ሰንበትን በማርከሳችሁ በእስራኤል ላይ መዓትን ትጨምራላችሁ አልኋቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ነህምያ 13:18
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የምድሪቱ ሕዝቦች ሸቀጥ ወይም ልዩ ልዩ እህል ለመሸጥ በሰንበት ቀን ቢያመጡ፥ በሰንበት ወይም በተቀደሰ ቀን ከእነርሱ አንገዛም፤ በሰባተኛው ዓመትም ምድሪቱን እናሳርፋታለን፥ ዕዳንም ሁሉ እንሰርዛለን።


ጌታ ሙሴን እንዲህ አለው፦


ነገር ግን የሰንበትን ቀን እንድትቀድሱ፥ በሰንበትም ቀን ሸክምን ተሸክማችሁ በኢየሩሳሌም በሮች እንዳትገቡ የነገርኋችሁን ባትሰሙኝ፥ በበሮችዋ ላይ እሳትን አነድዳለሁ፥ የኢየሩሳሌምንም የንጉሥ ቅጥሮች ትበላለች፥ አትጠፋምም።’ ”


ጌታም ከእንግዲህ ወዲህ የሥራችሁን ክፋትና ያደረጋችሁትን ርኩሰት መታገሥ አልቻለም፤ ስለዚህ ምድራችሁ ባድማ መሣቀቂያም መረገሚያም ሆናለች ዛሬም እንደሆነ የሚኖርባት የለም።


ስላጠናችሁ፥ በጌታም ላይ ኃጢአትን ስለ ሠራችሁ፥ የጌታንም ድምፅ ስላልሰማችሁ፥ በሕጉና በሥርዓቱም በምስክሩም ስላልሄዳችሁ፥ ስለዚህ ዛሬ እንደሆነ ይህ ክፉ ነገር ደርሶባችኋል።”


በውኑ በይሁዳ ምድርና በኢየሩሳሌም አደባባይ ያደረጉትን የአባቶቻችሁን ክፋት፥ የይሁዳንም ነገሥታት ክፋት፥ የሚስቶቻቸውንም ክፋት፥ የእናንተንም ክፋት፥ የሚስቶቻችሁንም ክፋት ረስታችሁታልን?


ልብስሽን ይገፍፉሻል የሚያማምሩ ጌጣጌጦችሽን ይወስዳሉ።


ከግብጽ ጀምሮ የነበረውን አመንዝራነቷን አልተወችም፤ በወጣትነትዋ ጊዜ ወንዶች ከእርሷ ጋር ተኝተው ነበርና፥ የድንግልናዋንም የጡቶቿ ጫፎች ዳብሰው ነበርና፥ ፍትወታቸውንም አፍስሰውባት ነበርና።


እነዚህም ነገሮች ተደርገውባችሁ እንኳ ባትሰሙኝ፥ ስለ ኃጢአታችሁ ሰባት እጥፍ ጨምሬ ዳግመኛ እቀጣችኋለሁ።


እኔ ደግሞ በቁጣ እናንተን በመቃወም እሄዳለሁ፤ እኔም ስለ ኃጢአታችሁ ሰባት እጥፍ እቀጣችኋለሁ።


እናንተ እንዲህ ትላላችሁ፦ “እህልን እንድንሸጥ መባቻው መቼ ያልፋል? ስንዴውንም ለሽያጭ ገበያ ለማቅረብ ሰንበት መቼ ያበቃል? የኢፍ መስፈሪያውንም እናሳንሳለን፥ ሰቅሉንም እናበዛለን፥ በሐሰተኛም ሚዛን እናታልላለን፥


እነሆም፥ የጌታን መዓት በእስራኤል ላይ አብዝታችሁ ለመጨመር እናንተ የኃጢአተኞች ትውልድ በአባቶቻችሁ ፋንታ ተነሣችሁ!


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች