ነህምያ 12:38 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)38 ከፊት ይሄድ የነበረው ሁለተኛው የምስጋና መዘምራን ክፍል ነበር፤ እኔና የሕዝቡ እኩሌታ በስተ ኋላቸው ነበርን፤ በቅጥሩም ላይ፥ ከ “የእቶኑ ግንብ” በላይ እስከ “ሰፊው ቅጥር” ድረስ፥ ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም38 ምስጋና የሚያቀርቡት ሁለተኛው ቡድን በስተግራ በኩል ሄደ፤ እኔም ከከፊሉ ሕዝብ ጋራ ሆኜ በቅጥሩ ግንብ ላይ፣ የእቶኑን ግንብ በማለፍ እስከ ሰፊው ቅጥር ተከተልኋቸው፤ ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም38 ሌላው የመዘምራን ቡድን ሰልፍ የቅጽሩን ግንብ ጫፍ በመከተል ወደ ግራ በኩል አለፈ፤ እኔም ከሕዝቡ እኩሌታ ጋር ይህንኑ የቡድን ሰልፍ እከተል ነበር፤ የእቶኑንም ግንብ አልፈን ወደ ሰፊው ቅጽር ግንብ ደረስን። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)38 ሁለተኛውም የአመስጋኞቹ ክፍል ወደ ግራ ሄደ፤ እኔና የሕዝቡም እኩሌታ በስተኋላቸው ነበርን፤ በቅጥሩም ላይ፥ በእቶኑ ግንብ በላይ እስከ ሰፊው ቅጥር ድረስ፥ ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)38 ሁለተኛውም የአመስጋኞቹ ተርታ ወደ ግራ ሄደ፥ እኔና የሕዝቡም እኩሌታ በስተኋላቸው ነበርን፥ በቅጥሩም ላይ፥ በእቶኑ ግንብ በላይ እስከ ሰፊው ቅጥር ድረስ፥ ከኤፍሬምም በር በላይ፥ ምዕራፉን ተመልከት |