ነህምያ 12:31 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)31 የይሁዳንም አለቆች ወደ ቅጥሩ ላይ አወጣኋቸው፥ አመስጋኞቹንም በሁለት ታላላቅ ተርታ አቆምኋቸው፥ አንዱም ወደ ቀኝ በቅጥሩ ላይ ወደ ጉድፍ መጣያው በር ሄደ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም31 እኔም የይሁዳን መሪዎች በቅጥሩ ግንብ ዐናት ላይ እንዲወጡ አደረግሁ፤ ደግሞም ምስጋና እንዲያቀርቡ ሁለት ታላላቅ የመዘምራን ቡድን መደብሁ። አንዱ በቅጥሩ ግንብ ዐናት በስተቀኝ በኩል ቈሻሻ መጣያ በር ወደሚባለው ሄደ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም31 እኔም ነህምያ የይሁዳን መሪዎች በቅጽሩ ላይ እንዲወጡ ካደረግሁ በኋላ ሁለት ታላላቅ የመዘምራን ቡድን የምስጋና መዝሙር እንዲዘምሩ አደረግሁ፤ የመጀመሪያው ቡድን በቅጽሩ ግንብ አናት ላይ በስተቀኝ በኩል ወደሚገኘው ወደ ጒድፍ መጣያው የቅጽር በር በኩል አለፈ፤ ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)31 የይሁዳንም አለቆች ወደ ቅጥሩ አወጣኋቸው፤ አመስጋኞቹንም በሁለት ታላላቅ ተርታ አቆምኋቸው፤ የአንዱም ተርታ ሰዎች ወደ ቀኝ በቅጥሩ ላይ ወደ ጉድፍ መጣያው በር ሄዱ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)31 የይሁዳንም አለቆች ወደ ቅጥሩ ላይ አወጣኋቸው፥ አመስጋኞቹንም በሁለት ታላላቅ ተርታ አቆምኋቸው፥ አንዱም ወደ ቀኝ በቅጥሩ ላይ ወደ ጕድፍ መጣያው በር ሄደ። ምዕራፉን ተመልከት |