Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ነህምያ 12:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 እነዚህ በዮፃዳቅ ልጅ በኢያሱ ልጅ በዮያቂም ዘመንና በገዢው በነህምያና በጸሐፊው በካህኑ በዕዝራ ዘመን ነበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 እነዚህም በኢዮሴዴቅ ልጅ፣ በኢያሱ ልጅ በዮአቂም፣ በአገረ ገዥ በነህምያ፣ በካህኑና በጸሓፊው በዕዝራ ዘመን አገለገሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 እነዚህም የኢዮጼዴቅ የልጅ ልጅ የሆነው የኢያሱ ልጅ ዮያቂም፥ አገረ ገዢው ነህምያ ካህኑና የሕግ ሊቁ ዕዝራ በነበሩበት ዘመን የተመደቡ አገልጋዮች ነበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 እነ​ዚ​ህም በኢ​ዮ​ሴ​ዴቅ ልጅ በኢ​ያሱ ልጅ በዮ​አ​ቂም በአ​ለ​ቃ​ውም በነ​ህ​ምያ፥ በጸ​ሓ​ፊ​ውም በካ​ህኑ በዕ​ዝራ ዘመን ነበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 እነዚህ በኢዮሴዴቅ ልጅ በኢያሱ ልጅ በዮአቂም በአለቃውም በነህምያ በጸሐፊውም በካህኑ በዕዝራ ዘመን ነበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ነህምያ 12:26
5 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ገዢው ነህምያ፥ ጸሐፊው ካህኑ ዕዝራ፥ ሕዝቡን የሚያስተምሩ ሌዋውያን ሕዝቡን ሁሉ፦ “ይህ ቀን ለጌታ አምላካችሁ ቅዱስ ነው፤ አታልቅሱ እንባም አታፍስሱ” አሉአቸው፤ ሕዝቡ ሁሉ የሕጉን ቃል በሰሙ ጊዜ ያለቅሱ ነበርና።


የጌታን ትእዛዝ ቃልና ለእስራኤል የሆነውን ሥርዓት ይጽፍ ለነበረው ለጸሐፊው ለካህኑ ለዕዝራ ንጉሡ አርጤክስስ የሰጠው የደብዳቤው ግልባጭ ይህ ነው፦


ይህ ዕዝራ ከባቢሎን መጣ፥ የእስራኤል አምላክ ጌታ ለሙሴ በሰጠው ሕግ ችሎታ ያለው ጸሐፊ ነበረ፤ የአምላኩ የጌታ እጅ በእርሱ ላይ ስለ ነበረች ንጉሡ የጠየቀውን ነገር ሁሉ ሰጠው።


ከኤፍራጥስም ወንዝ ጀምሮ እስከ ፍልስጥኤም ምድርና እስከ ግብጽ ዳርቻ ድረስ ባሉ ነገሥታት ሁሉ ላይ ነገሠ።


ሕዝቡም ሁሉ በውኃው በር ፊት ወዳለው አደባባይ እንደ አንድ ሰው ሆነው ተሰበሰቡ፤ ጌታ ለእስራኤል ያዘዘውን የሙሴን ሕግ መጽሐፍ እንዲያመጣ ለጸሐፊው ለዕዝራ ነገሩት።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች