ነህምያ 12:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)22 ከሌዋውያኑም በኤልያሺብ፥ ዮያዳዕ፥ ዮሐናን፥ ያዱዓ ዘመን የአባቶች መሪዎችና ካህናቱ በፋርሳዊው በዳርዮስ ዘመነ መንግሥት ተመዝግበው ነበር። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም22 በኤልያሴብ፣ በዮአዳ፣ በዮሐናንና በያዱአ ዘመን የሌዋውያኑ ቤተ ሰብ አለቆችና ካህናቱ፣ በፋርሳዊው በዳርዮስ ዘመነ መንግሥት ተመዝግበው ነበር። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም22 ኤልያሺብ፥ ዮያዳዕ፥ ዮናታንና ያዱዐ ተብለው የሚጠሩት ሊቃነ ካህናት በኖሩበት ዘመን የሌዋውያንና የካህናት ቤተሰብ አለቆች ተለይተው የሚታወቁበት መዝገብ ተዘጋጅቶ ነበር፤ ይህም መዝገብ የተዘጋጀው ዳርዮስ የፋርስ ንጉሠ ነገሥት በሆነበት ዘመን ነበር። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)22 ከሌዋውያኑም በኤልያሴብና በዮሐዳ፥ በዮሐናንና በያዱዕ ዘመን የአባቶች ቤቶች አለቆች ተጻፉ፤ ካህናቱም በፋርሳዊው በዳርዮስ መንግሥት ዘመን ተጻፉ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)22 ከሌዋውያኑም በኤልያሴብና በዮአዳ፥ በዮሐናንና በያዱአ ዘመን የአባቶች ቤቶች አለቆች ተጻፉ፥ ካህናቱም በፋርሳዊው በዳርዮስ መንግሥት ዘመን ተጻፉ። ምዕራፉን ተመልከት |