Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ነህምያ 11:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 በሜዳዎቻቸው ስለ ነበሩ ስለ መንደሮቻቸው፦ ከይሁዳ ልጆች አንዳንዶቹ በእነዚህ ቦታዎች ተቀመጡ፦ በቂርያት አርባዕና በመንደሮችዋ፥ በዲቦንና በመንደሮችዋ፥ በይቃብጽኤልና በመንደሮችዋ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 ከይሁዳ ሕዝብ ጥቂቱ በመንደሮችና በዕርሻ ቦታዎች፣ በቂርያት አርባቅና በዙሪያዋ ባሉ መኖሪያዎቿ፣ በዲቦንና በመኖሪያዎቿ፣ በይቀብጽኤልና በመንደሮቿ ተቀመጡ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 መንደሮቹንና እርሻዎቹን በተመለከተ ከይሁዳ ነገድ መካከል አንዳንዶቹ በቂርያት አርባዕና በመንደሮችዋ፥ በጊቦንና በመንደሮችዋ በይቀብጽኤልና በመንደሮችዋ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 ስለ መን​ደ​ሮ​ቹና ስለ እር​ሻ​ዎ​ቻ​ቸው ከይ​ሁዳ ልጆች ዐያ​ሌ​ዎች በቂ​ር​ያ​ት​አ​ር​ባ​ቅና በመ​ን​ደ​ሮ​ችዋ፥ በዲ​ቦ​ንና በመ​ን​ደ​ሮ​ች​ዋም፥ በቃ​ጽ​ብ​ኤ​ልና በመ​ን​ደ​ሮ​ች​ዋም፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 ስለ መንደሮቹና ስለ እርሾቻቸው፥ ከይሁዳ ልጆች አያሌዎች በቂርያትአርባቅና በመንደሮችዋ፥ በዲቦንና በመንደሮችዋም፥ በይቀብጽኤልና በመንደሮችዋም፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ነህምያ 11:25
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በከነዓንም ምድር ባለችው ቂርያት-አርባዕ ተብላ በምትጠራው በኬብሮን ከተማ ሞተች፤ አብርሃምም ለሣራ ሊያዝንላትና ሊያለቅስላት ተነሣ።


በኢያሱ፥ በሞላዳ፥ በቤት ጳሌጥ፥


ሐሴቦንም፥ በሜዳውም ያሉት ከተሞችዋ ሁሉ፥ ዲቦን፥ ባሞትበኣል፥ ቤትባኣልምዖን፥


በአርኖን ሸለቆ ዳር ካለችው ከአሮዔር፥ በሸለቆውም መካከል ካለችው ከተማ ጀምሮ የሜድባን ሜዳ ሁሉ እስከ ዲቦን ድረስ፥


ኢያሱም ባረከው፤ ለዮፎኒም ልጅ ለካሌብ ኬብሮንን ርስት አድርጎ ሰጠው።


የኬብሮንም ስም አስቀድሞ ቂርያት-አርባቅ ትባል ነበር፤ ይህም አርባቅ በዔናቅ ሰዎች መካከል ታላቅ ሰው ነበረ። ምድሪቱም ከውጊያ ዐረፈች።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች