Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ነህምያ 11:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 በእግዚአብሔር ቤት ሥራ ላይ ከነበሩ መዘምራን ከአሳፍ ልጆች ወገን የሚካ ልጅ፥ የማታንያ ልጅ፥ የሓሻብያ ልጅ፥ የባኒ ልጅ ዑዚ በኢየሩሳሌም የሌዋውያን አለቃ ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 በኢየሩሳሌም የሌዋውያኑ ዋና አለቃ የሚካ ልጅ፣ የመታንያ ልጅ፣ የሐሸብያ ልጅ፣ የባኒ ልጅ ኦዚ ነበረ፤ ኦዚ በእግዚአብሔር ቤት አገልግሎት ለሚዘመረው መዝሙር ኀላፊ ከነበሩት ከአሳፍ ዘሮች አንዱ ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 በኢየሩሳሌም የሌዋውያን አለቃ ዑዚ የባሂ ልጅ፥ የሖሻብያ ልጅ፥ የማታንያ ልጅ፥ የሚካ ልጅ ነበር። ዑዚ የቤተ መቅደስ መዘምራን ኀላፊ የነበረው የአሳፍ ዘር ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት ሥራ ላይ ከነ​በሩ መዘ​ም​ራን ከአ​ሳፍ ልጆች ወገን የሚካ ልጅ፥ የመ​ታ​ንያ ልጅ፥ የሐ​ሳ​ብያ ልጅ፥ የባኒ ልጅ ኦዚ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የሌ​ዋ​ው​ያን አለቃ ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 በእግዚአብሔርም ቤት ሥራ ላይ ከነበሩ መዘምራን ከአሳፍ ልጆች ወገን የሚካ ልጅ የመታንያ ልጅ የሐሸብያ ልጅ የባኒ ልጅ አዚ በኢየሩሳሌም የሌዋውያን አለቃ ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ነህምያ 11:22
19 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

መዕሤያ፥ ሽማዕያ፥ አልዓዛር፥ ኡዚ፥ ይሆሐናን፥ ማልኪያ፥ ዔላም፥ ዓዜር ቆምን። መዘምራኑም በዪዝራሕያ መሪነት በታላቅ ድምፅ ዘመሩ።


መለከት የያዙ ጥቂት የካህናቱ ልጆች፥ የአሳፍ ልጅ፥ የዛኩር ልጅ፥ የሚካያ ልጅ፥ የማታንያ ልጅ፥ የሸማዕያ ልጅ፥ የዮናታን ልጅ ዘካርያስ፥


ወንድሞቻቸው መቶ ሀያ ስምንት ጽኑዓን ኃያላን፤ አለቃቸውም የሃግዶሊም ልጅ ዛብዲኤል ነበረ።


የእግዚአብሔር ቤት አለቃ የአሒጡብ ልጅ የምራዮት ልጅ፥ የጻዶቅ ልጅ የምሹላም ልጅ፥ የሒልቂያ ልጅ ሥራያ፥


አለቃቸውም የዚክሪ ልጅ ኢዮኤል ነበር፤ የሃስኑአ ልጅ ይሁዳ ደግሞ በከተማው ላይ ሁለተኛ የተሾመ ነበረ።


ዛኩር፥ ሼሬብያ፥ ሽባንያ፥


ወንድሞቻቸው ሽባንያ፥ ሆዲያ፥ ቅሊጣ፥ ፕላያ፥ ሐናን፥


ደግሞ ኢያሱ፥ ባኒ፥ ሼሬብያ፥ ያሚን፥ ዓቁብ፥ ሻብታይ፥ ሆዲያ፥ ማዓሤያ፥ ቅሊጣ፥ አዛርያ፥ ዮዛባድ፥ ሐናን፥ ፐላያና ሌዋውያኑ ሕጉን ለሕዝቡ ያስረዱ ነበር፤ ሕዝቡም በቆሙበት ነበሩ።


ከእርሱም በኋላ ሌዋውያንና የባኒ ልጅ ሬሑም አደሱ። በአጠገቡ የቅዒላ አውራጃ እኩሌታ ገዢ ሐሻብያ ስለ አውራጃው ብሎ አደሰ።


እንዲሁም ሐሻብያ ከእርሱም ጋር ከሜራሪ ልጆች ወገን የነበረውን ይሻዕያና ወንድሞቹንና ልጆቻቸው ሀያ ወንዶች።


በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ኤጲስ ቆጶሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።


በዕቃ ቤቶችም ላይ ካህኑን ሰሌምያን፥ ጸሐፊውንም ሳዶቅን፥ ከሌዋውያኑም ፈዳያን ሾምሁ፥ ከእነርሱም ጋር የማታንያ ልጅ የዘኩር ልጅ ሐናን ነበረ፥ እነርሱም የታመኑ ሆነው ተገኙ፥ ሥራቸውም ለወንድሞቻቸው ማከፋፈል ነበረ።


አስቀድሞም በዳዊትና በአሳፍ ዘመን እግዚአብሔርን በዜማ ለማመስገንና ለማክበር የመዘምራን አለቆች ነበሩ።


መፊቦሼት ሚካ የተባለ አንድ ትንሽ ልጅ ነበረው፤ የጺባ ቤተሰቦች በሙሉ መፊቦሼትን ያገለግሉት ነበር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች