ናሆም 3:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)8 አንቺ በዓባይ ፈሳሾች መካከል ከተቀመጠችው፥ ውኃም በዙሪያዋ ከነበራት፥ ምሽግዋም ባሕር ከነበረ፥ ቅጥርዋም በባሕር ውስጥ ከነበረ ከኖእ አሞን ትበልጫለሽን? ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም8 አንቺ በአባይ ወንዝ አጠገብ ካለችው፣ በውሃ ከተከበበችው፣ ከኖእ አሞን ትበልጫለሽን? ወንዙ መከላከያዋ፣ ውሃውም ቅጥሯ ነው። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም8 ነነዌ ሆይ! አንቺም የውሃ መከላከያ እንዳለሽ ሁሉ በአባይ ወንዝ አጠገብ ከነበረችው፥ ዙሪያዋ በውሃ ከተከበበው፥ የባሕር ውሃም መከላከያዋ ከሆነው ከግብጽ ከተማ ከቴብስ ትበልጫለሽን? ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)8 አንቺ በመስኖች መካከል ከተቀመጠችው፥ ውኃም በዙሪያዋ ከነበራት፥ ምሽግዋም ባሕር ከነበረ፥ ቅጥርዋም በባሕር ውስጥ ከነበረ ከኖእ አሞን ትበልጫለሽን? ምዕራፉን ተመልከት |