Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ናሆም 3:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ርኩሰትንም በላይሽ ልይ እጥላለሁ፥ እንቅሻለሁ፥ ማላገጫም አደርግሻለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ቈሻሻ እደፋብሻለሁ፤ እንቅሻለሁ፤ ማላገጫም አደርግሻለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 የቈሻሻ መጣያ አደርግሻለሁ፤ በንቀት እመለከትሻለሁ፤ ሰው ሁሉ እንዲሳለቅብሽ አደርጋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ርኵሰትንም በላይሽ እጥላለሁ፥ እንቅሽማለሁ፥ ማላገጫም አደርግሻለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ናሆም 3:6
19 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ስለዚህ መንገዴን ስላልጠበቃችሁ፥ በሕግም ለሰው ፊት እንዳዳላችሁ መጠን፥ እኔ ደግሞ በሕዝብ ሁሉ ፊት የተናቃችሁና የተዋረዳችሁ አድርጌአችኋለሁ።


ባቢሎንም የፍርስራሽ ክምር፥ የቀበሮ ማደሪያ ሰውም የማይቀመጥባት መሣቀቅያና ማፍዋጫ ትሆናለች።


በአዘቅት ውስጥ ታሰጥመኛለህ፥ ልብሴም ይጸየፈኛል።


አንዳንድ ጊዜ በግላጭ ለነቀፋና ለስደት የተዳረጋችሁ ነበራችሁ፤ አንዳንዴም እንዲህ ካሉት ጋር በሚደርስባቸው ነገር ተካፋይ ሆናችሁ ነበር፤


እግዚአብሔር እኛን ሐዋርያቱን ሞት እንደ ተፈረደባቸው ሰዎች ከሁሉ ይልቅ የኋለኞች እንዳደረገን ይመስለኛል፤ ምክንያቱም ለዓለም ለመላእክትም ለሰዎችም ትንግርት ሆነናል።


ጌታ ከእንግዲህ ወዲህ በስምህ እንዳይዘራ ስለ አንተ አዝዞአል፤ ከአምላኮችህ ቤት ጣዖትንና ቀልጦ የተሠራውን ምስል አጠፋለሁ። አንተም የማትረባ ነህና መቃብርህን እምሳለሁ።


የአላዋቂና የነውረኞች ልጆች ናቸው፥ ከምድርም በግርፋት የተባረሩ ናቸው።”


እንዲሁም ሰዶምና ገሞራ በዙሪያቸውም የነበሩ ከተማዎች፥ እንደ እነርሱ ዝሙትን ያደረጉና ሌላን ሥጋ የተከተሉ በዘለዓለም እሳት እየተቀጡ ምሳሌ ሆነዋል።


ክፉ ሲናገሩን በትሕትና እንመልስላቸዋለን፤ እስከ አሁን ድረስ የዚህ ዓለም ጥራጊ የሁሉም ጉድፍ ሆነናል።


“ባትሰሙ፥ ለስሜም ክብር ለመስጠት በልባችሁ ባታኖሩት፥” ይላል የሠራዊት ጌታ፥ “እርግማን እልክባችኋለሁ፥ በረከታችሁንም እረግማለሁ፤ አሁንም ረግሜዋለሁ ምክንያቱም በልባችሁ አላደረጋችሁትምና።”


ስጋት ሳይኖርባት የተቀመጠች ደስተኛይቱ ከተማ ይህች ናት፥ በልብዋም፦ “እኔ ነኝ፥ ከእኔም በቀር ሌላ የለም” ያለች፥ እንዴት አራዊት የሚመሰጉባት ባድማ ሆነች! በእርሷ በኩል የሚያልፈው ሁሉ እጁን እያወዛወዘ ያፏጫል።


ዋው። ጥርሴን በጭንጫ ሰበረ፥ በአመድም ከደነኝ።


በጭቃ ውስጥ ጣለኝ፥ አፈርና አመድም መሰልሁ።


ስለዚህ እነሆ እኔ ደስ የተሰኘሽባቸውን ወዳጆችሽን ሁሉ፥ የወደድሻቸውን ሁሉ ከጠላሻቸው ሁሉ ጋር እሰበስባቸዋለሁ፤ ሁሉንም ከየአቅጣጫው በአንቺ ላይ እሰበስባቸዋለሁ፥ ራቁትነትሽን ሁሉ እንዲያዩ በፊታቸው ዕርቃንሽን እገልጣለሁ።


በክብር ፈንታ እፍረት ሞልቶብሃል፤ አንተ ደግሞ ጠጣ፥ እንዳልተገረዘም ተቆጠር፤ የጌታ የቀኙ ጽዋ በአንተ ላይ ይመለስብሃል፥ እፍረትም በክብርህ ላይ ይሆናል።


እነሆ፥ ዘራችሁን እገሥጻለሁ፥ በፊታችሁ ላይ ፈርስን እበትናለሁ፥ ይህም ፈርስ ለበዓላችሁ መሥዋዕት ካመጣችኋቸው ነው፤ እናንተንም ከእርሱ ጋር ያነሳችኋል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች