Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ናሆም 3:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 የአሦር ንጉሥ ሆይ፥ እረኞችህ አንቀላፍተዋል፤ መኳንንቶችህም ዐርፈዋል፤ ሕዝብህ በተራሮች ላይ ተበትነዋል፥ የሚሰበስባቸውም የለም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 የአሦር ንጉሥ ሆይ፤ እረኞችህ አንቀላፉ፤ መኳንንትህ ዐርፈው ተኙ፤ ሕዝብህ ሰብሳቢ ዐጥተው፣ በተራራ ላይ ተበትነዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 የአሦር ንጉሥ ሆይ፥ ጠባቂዎችህ ተኝተዋል፤ ልዑላንህ አንቀላፍተዋል፤ ሕዝብህ በተራራ ላይ ተበትነዋል፤ የሚሰበስባቸውም የለም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 የአሦር ንጉሥ ሆይ፥ እረኞችህ አንቀላፍተዋል፣ መኳንንቶችህም ዐርፈዋል፣ ሕዝብህም በተራሮች ላይ ተበትኖአል፥ የሚሰበስበውም የለም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ናሆም 3:18
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሚክያስም “መላው የእስራኤል ሠራዊት ጠባቂ እንደሌላቸው በጎች በኮረብታዎች ላይ ተበታትነው አያለሁ፤ ጌታም ‘እነዚህ ሰዎች መሪ የላቸውም፤ ስለዚህ ወደየቤታቸው በሰላም ይመለሱ ብሏል’ ሲል መለሰለት።”


ሕዝብህ እስኪያልፍ ድረስ፥ ጌታ ሆይ የገዛኸው ሕዝብ እስኪያልፍ ድረስ፥ በኃይልህ ታላቅነት፥ ፍርሃትና ድንጋጤ ወደቀባቸው፥ እንደ ድንጋይ ቀጥ አሉ።


እንደሚታደን ሚዳቋ፤ እረኛም እንደሌለው የበግ መንጋ፤ እያንዳንዱ ወደ ወገኑ ይመለሳል፤ እያንዳንዱም ወደ አገሩ ይሸሻል።


አንቺ ድንግል የባቢሎን ልጅ ሆይ፥ ውረጂ በትቢያም ላይ ተቀመጪ፤ የከለዳውያን ሴት ልጅ ሆይ ከዚህ በኋላ ቅንጡና ቅምጥል አትባይምና ያለ ዙፋን በመሬት ላይ ተቀመጪ።


ስለዚህ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ የአሦርን ንጉሥ እንደ ቀጣሁ እንዲሁ፥ እነሆ፥ የባቢሎንን ንጉሥና ምድሩን እቀጣለሁ።


ሞቅ ባላቸው ጊዜ ደስ እንዲላቸው ለዘለዓለምም አንቀላፍተው እንዳይነቁ የመጠጥ ግብዣ አደርግላቸዋለሁ አሰክራቸዋለሁም፥ ይላል ጌታ።


አለቆችዋንና ጥበበኞችዋንም፥ ገዢዎችዋንና ሹማምቶችዋን ኃያላኖችዋንም አሰክራለሁ፥ ለዘለዓለምም አንቀላፍተው አይነቁም፥ ይላል ስሙ የሠራዊት ጌታ የተባለው ንጉሥ።


የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም፥ ሀብታሞችም፥ ኃይለኞችም፥ አገልጋዮችም፥ ጌቶችም ሁሉ በዋሻዎችና በተራራዎች ዐለቶች ውስጥ ተሰወሩ፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች