Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ናሆም 3:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ጠባቂዎችሽ እንደ አንበጣ፥ መኳንንቶችሽም በብርድ ቀን በቅጥር ላይ እንደ ሰፈረ የኩብኩባ መንጋ ናቸው፤ ፀሐይም በወጣች ጊዜ ይበራሉ፥ ስፍራቸው የት እንደሆነ አይታወቅም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ጠባቂዎችሽ እንደ አንበጣ፣ መኳንንትሽም በብርድ ቀን በቅጥር ሥር እንደሚቀመጥ ኵብኵባ ናቸው፤ ፀሓይ ሲወጣ ግን ይበርራሉ፤ ወዴት እንደሚበርሩም አይታወቅም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ጠባቂዎችሽ እንደ ኲብኲባ፥ ባለ ሥልጣኖችሽ በብርድ ቀን በአጥር ላይ እንደ ሰፈረ የአንበጣ መንጋ ናቸው፤ ፀሐይ ሲወጣ በረው ይሄዳሉ፤ ወዴት እንደሚሄዱ ግን የሚያውቅ የለም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 በአንቺ ዘንድ ዘውድ የጫኑት እንደ አንበጣ፥ አለቆችሽም እንደሚንቀሳቀሱ ኩብኩባዎች ናቸው፣ በብርድ ቀን በቅጥር ውስጥ ይቀመጣሉ፥ ፀሐይም በወጣች ጊዜ ያኰበኵባሉ፣ ስፍራቸው በየት እንደ ሆነ አይታወቅም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ናሆም 3:17
4 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በምድር ላይ ዓላማን አንሡ በአሕዛብም መካከል መለከት ንፉ፥ አሕዛብንም ለጦርነት በእርሷ ላይ አዘጋጁ፤ የአራራትንና የሚኒን የአስከናዝንም መንግሥታት ጥሩባት አለቃንም በእርሷ ላይ ሹሙ፤ እንደ ጠጉራም ኩብኩባ ፈረሶችን በእርሷ ላይ አውጡ።


ባዕዳን፥ የሕዝቦች ጨካኞች የሆኑ፥ ቆርጠው ጣሉት፤ በተራሮች እና በሸለቆዎች ሁሉ ውስጥ ቅርጫፎቹ ወደቁ፥ ቅርንጫፎቹም በምድር ፈሳሾች ሁሉ ላይ ተሰባበሩ፥ የምድርም ሕዝቦች ሁሉ ከጥላው ወጥተው ትተውት ሄዱ።


ነነዌ በዘመኗ ሁሉ እንደ ተከማቸ ውኃ ነበረች፤ እርሱም እየደረቀ ነው። “ቁሙ፥ ቁሙ” ይላሉ፥ ነገር ግን የሚመለስ የለም።


አንበጣዎቹም ለጦርነት የተዘጋጁ ፈረሶችን ይመስሉ ነበር፤ በራሳቸውም ላይ የወርቅ የሚመስሉ አክሊሎች ነበሩአቸው፤ ፊታቸውም የሰው ፊት ይመስል ነበረ፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች