Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ናሆም 2:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 አሁን ታድያ የአንበሶቹ ዋሻ፥ ደቦሎቻቸውን ያበሉበት፥ ወንዱና ሴቷ አንበሳ የሄዱበት፥ ግልገሎቹም ሳይፈሩ የተሰማሩበት ወዴት ነው?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 አንበሳው ለግልገሎቹ የሚበቃውን ያህል ገደለ፤ ለእንስቶቹም ዐንቆ ገደለላቸው፤ የገደለውን በማረፊያ ቦታው፣ የነጠቀውንም በዋሻው ሞልቶታል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 አንበሳ ለግልገሎቹ የሚበቃቸውን ያኽል ዐድኖ አመጣ፤ ለእንስቲቱ አንበሳም የምትመገበውን ገድሎ አመጣላት፤ ዋሻውን በታደኑ እንስሶች ጒድጓዱንም በተቦጫጨቀ ሥጋ ሞላ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 አንበሳው ለልጆቹ የሚበቃውን ነጠቀ፥ ለእንስቶቹም ሰበረላቸው ዋሻውን በንጥቂያ፥ መደቡንም በቅሚያ ሞልቶታል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ናሆም 2:12
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሑሻይም በተጨማሪ እንዲህ አለው፥ “አባትህና ሰዎቹ ብርቱ ጦረኞችና ግልገሎችዋም እንደተነጠቁባት የዱር ድብ አምርረው የሚነሡ መሆኑን ታውቃለህ፤ በተጨማሪም አባትህ በጦር ሜዳ ልምድ ያለው ነው፤ ሌሊቱን ከሠራዊቱ ጋር አያድርም፤


እርሱ ንጥቂያን እንደሚናፍቅ አንበሳ ተሸጉጦም እንደሚኖር እንደ አንበሳ ደቦል ነው።


የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር በላኝ፥ አደቀቀኝም፥ እንደ ባዶ ዕቃም አደረገኝ፥ እንደ ዘንዶም ዋጠኝ፥ ከሚጣፍጠውም ምግቤ ሆዱን ሞላ፥ እኔንም አውጥቶ ተፋኝ።


ባዶ፥ ባድማና የጠፋች ሆናለች፥ ልብ ቀልጦአል፥ ጉልበቶች ተብረክርከዋል፤ በወገብም ሁሉ ሕማም አለ፥ የሁሉም ፊት ጠቁሮአል።


አንበሳው ለልጆቹ የሚበቃውን ያህል ነጠቀ፥ ለእንስቶቹም አነቀላቸው፥ ዋሻውን በነጠቀው፥ ጉድጓዱንም በተቦጫጨቀ ሥጋ ሞልቶታል።


እነሆ፥ ሕዝቡ እንደ እንስት አንበሳ ብድግ ይላል፥ እንደ አንበሳም ይነሣል፤ ያደነውን እስኪበላ፥ የገደለውንም ደሙን እስኪጠጣ አያርፍም።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች