Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ናሆም 2:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ባዶ፥ ባድማና የጠፋች ሆናለች፥ ልብ ቀልጦአል፥ ጉልበቶች ተብረክርከዋል፤ በወገብም ሁሉ ሕማም አለ፥ የሁሉም ፊት ጠቁሮአል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 አሁን ታዲያ የአንበሶቹ ዋሻ፣ ደቦሎቻቸውን ያበሉበት ወንዱና ሴቷ አንበሳ የሄዱበት፣ ግልገሎችም ሳይፈሩ የተሰማሩበት ቦታ ወዴት ነው?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 አንበሶች የሚኖሩበትን፥ የአንበሶች ደቦሎች የሚመገቡበትን፥ ወንድና ሴት አንበሶች ከግልገሎቻቸው ጋር ያለ ስጋት የሚዝናኑበትን መስክ ትመስል የነበረችው፥ ያቺ ከተማ አሁን የት አለች?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 የአንበሾችም መደብ፥ የአንበሾችም ደቦል የሚሰማራበት፥ አንበሳውና አንበሳይቱ ግልገሉም ሳይፈሩ የሚሄዱት ስፍራ ወዴት ነው?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ናሆም 2:11
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ይሁዳ የአንበሳ ደቦል ነው፥ ልጄ ሆይ፥ ከአደንህ ወጣህ፥ እንደ አንበሳ አሸመቀ፥ እንደ ሴት አንበሳም አደባ፥ ያስነሣውስ ዘንድ ማን ይችላል?


ስለዚህ እጆች ሁሉ ሽባ ይሆናሉ፤ የሰውም ሁሉ ልብ ይቀልጣል።


ጌታም እንዲህ ይለኛልና፦ አንበሳ ወይም የአንበሳ ደቦል በንጥቂያው ላይ ሲያገሣ፥ ብዙ እረኞች ቢከማቹበት ከቃላቸው እንደማይፈራ ከድምፃቸውም እንደማይዋረድ፥ እንደዚሁም የሠራዊት ጌታ በጽዮን ተራራና በኮረብታዋ ላይ ለመዋጋት ይወርዳል።


ጩኸታቸው እንደ አንበሳ ነው፤ እንደ አንበሳ ደቦል ያገሣሉ፤ ያደኑትንም ይዘው ይጮኻሉ፤ ተሸክመውት ይሄዳሉ፤ የሚያስጥልም የለም።


የአንበሳ ደቦሎች በእርሱ ላይ አገሡ፥ ድምፃቸውንም አሰሙ፤ ምድሩንም ባድማ አደረጉ፥ ከተሞቹም ፈርሰዋል የሚቀመጥባቸውም የለም።


አንበሳ ከችፍግ ዱሩ ወጥቶአል፥ አሕዛብንም የሚያጠፋ ተነሥቶአል፤ ምድርሽን ባድማ ለማድረግ ከስፍራው ወጥቶአል፥ ከተሞችሽም ሰው የሌለባቸው ፍርስራሾች ይሆናሉ።


እስራኤል የባዘነ በግ ነው፤ አንበሶች አሳደዱት፤ መጀመሪያ የአሦር ንጉሥ በላው፥ በመጨረሻም የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር አጥንቱን ቈረጠመው።


እነሆ፥ በጽኑ የበጎች በረት ላይ ከዮርዳኖስ ዱር ውስጥ እንደሚወጣ አንበሳ እንዲሁ እኔ ከእርሷ ዘንድ በድንገት አባርራቸዋለሁ፤ የተመረጠውንም ማንኛውንም ሰው በእርሷ ላይ እሾመዋለሁ፤ እንደ እኔ ያለ ማን ነው? ወይስ እኔን እንድመጣ የሚጠራኝ ማን ነው? ወይስ በፊቴ የሚቆም እረኛ ማን ነው?


የሰው ልጅ ሆይ፥ ስለ ግብጽ ንጉሥ ስለ ፈርዖን ሙሾ አውርድ፥ እንዲህም በለው፦ በሕዝቦች መካከል አንበሳ መሰልህ፥ እንደ ባሕር አውሬ ነበርህ፤ በወንዞችህም ገንፍለህ ወጥተሃል፥ ውኃውንም በእግርህ አደፍርሰሃል፥ ወንዞችህንም አሳድፈሃል።


ከፊታቸው አሕዛብ ይንቀጠቀጣሉ፥ የሰውም ፊት ሁሉ ይጠቁራል።


የያዕቆብ ትሩፍ በብዙ ሕዝቦች መካከል ከጌታ ዘንድ እንደሚመጣ ጠል፥ በሣር ላይ እንደሚወርድ ካፊያ፥ ሰውን እንደማይጠብቅ፥ የሰውን ልጆች በመጠበቅ እንደማይዘገይ ይሆናል።


አሁን ታድያ የአንበሶቹ ዋሻ፥ ደቦሎቻቸውን ያበሉበት፥ ወንዱና ሴቷ አንበሳ የሄዱበት፥ ግልገሎቹም ሳይፈሩ የተሰማሩበት ወዴት ነው?


ለደም ከተማ ወዮላት! በሁለንተናዋ ማታለልና ዘረፋ ሞልቶባታል፤ ንጥቂያ ከእርሷ አይርቅም።


በውስጧ የሚኖሩ ባለ ሥልጣኖቿ የሚያገሡ አንበሶች ናቸው፥ ፈራጆችዋም ለጠዋት ምንም የማያስቀሩ የማታ ተኩላዎች ናቸው።


እነሆ፥ ሕዝቡ እንደ እንስት አንበሳ ብድግ ይላል፥ እንደ አንበሳም ይነሣል፤ ያደነውን እስኪበላ፥ የገደለውንም ደሙን እስኪጠጣ አያርፍም።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች