ናሆም 1:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)12 ጌታ እንዲህ ይላል፦ ኃይለኞችና ብዙዎች ቢሆኑም ይቆረጣሉ፥ ያልፋልም። እኔም አስጨንቄሻለሁ፥ ነገር ግን ከእንግዲህ ወዲህ አላስጨንቅሽም። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም12 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ምንም ኀይለኞችና ብዙዎች ቢሆኑም፣ ይቈረጣሉ፤ ይጠፋሉም። ይሁዳ ሆይ፤ ከዚህ በፊት ባስጨንቅህም፣ ከእንግዲህ አላስጨንቅህም። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም12 እግዚአብሔር ለሕዝቡ ለይሁዳ እንዲህ ይላል፦ “አሦራውያን ኀይለኞችና ቊጥራቸው የበዛ ቢሆንም እንኳ ተደምስሰው እንዳልነበሩ ይሆናሉ። ሕዝቤ ሆይ! ከዚህ በፊት መከራ ያጸናሁባችሁ ቢሆንም እንኳ ከእንግዲህ ወዲህ ይህን አላደርግባችሁም። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)12 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ኃይለኞችና ብዙዎች ቢሆኑ እንዲሁ ይቈረጣሉ፥ እርሱም ያልቃል። እኔም አስጨንቄሃለሁ፥ ነገር ግን ከእንግዲህ ወዲህ አላስጨንቅህም። ምዕራፉን ተመልከት |