Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሚክያስ 7:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 በአትክልት ቦታ መካከል ባለው ጥሻ ብቻቸውን የተቀመጡት የርስትህን መንጋ፥ ሕዝብህን በበትርህ ጠብቅ፤ እንደ ቀደመው ዘመን በበሳንና በገለዓድ ይሰማሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ብቻቸውን በዱር ውስጥ፣ በለመለመ መስክ የሚኖሩትን፣ የርስትህ መንጋ የሆኑትን፣ ሕዝብህን በበትርህ ጠብቅ፤ እንደ ቀድሞው ዘመን፣ በባሳንና በገለዓድ ይሰማሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 እግዚአብሔር ሆይ! የአንተ መንጋ የሆነውን ሕዝብህን በሥልጣንህ ጠብቅ፤ እነርሱም በለመለመ አትክልት ቦታ መካከል በጫካ ውስጥ ብቻቸውን የሚኖሩ ናቸው፤ እንደ ቀድሞው ዘመን በባሳንና በገለዓድ እንዲመገቡ አድርጋቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 በቀርሜሎስ መካከል ባለው ዱር ብቻቸውን የተቀመጡት ሰዎችህ፥ የርስትህን በጎች፥ በበትርህ አግድ፥ እንደ ቀደመውም ዘመን በበሳንና በገለዓድ ይሰማሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 በቀርሜሎስ መካከል ባለው ዱር ብቻቸውን የተቀመጡት ሰዎችህ፥ የርስትህን በጎች፥ በበትርህ አግድ፥ እንደ ቀደመውም ዘመን በበሳንና በገለዓድ ይሰማሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሚክያስ 7:14
35 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ይህም ሰላም ይሆናል፤ አሦር ወደ ምድራችን ከመጣ፥ ምሽጎቻችንንም ከረገጠ፥ ሰባት እረኞችና ስምንት አለቆች እናስነሣበታለን።


የሚራራላቸውም ይመራቸዋልና፥ በውኃም ምንጮች በኩል ይነዳቸዋልና አይራቡም፥ አይጠሙም፥ የበረኅ ትኩሳት ወይም ፀሐይ አይጐዳቸውም።


“በዚያ ቀን የወደቀችውን የዳዊትን ድንኳን አነሣለሁ፥ የተናደውንም ቅጥርዋን እጠግናለሁ፤ የፈረሰውንም አድሳለሁ፥ እንደ ቀደመውም ዘመን እሠራታለሁ፤


መንጋውን እንደ እረኛ ያሰማራል፥ ጠቦቶቹን በክንዱ ሰብስቦ በብብቱ ይሸከማል፥ የሚያጠቡትንም በቀስታ ይመራል።


አንተም እንዲህ አለክ፦ በሠረገላዬ ብዛት ወደ ተራሮች ከፍታ፥ ወደ ሲባኖስ ጥግ ወጥቻለሁ፤ ረጃጅሞቹን ዝግባዎች፥ የተመረጡትን ጥንዶች እቈርጣለሁ፥ ወደ ከፍታውም ዳርቻ ወደ ቀርሜሎስ ዱር እገባለሁ፤


ጌታ እርሱ አምላክ እንደሆነ እወቁ፥ እርሱ ሠራን፥ እኛም የእርሱ ነን፥ እኛስ ሕዝቡ የማሰማርያውም በጎች ነን።


እርሱ አምላካችን ነውና፥ እኛ የማሰማርያው ሕዝብ የእጁም በጎች ነንና።


ሕዝብህን አድን፥ ርስትህንም ባርክ፥ ጠብቃቸው፥ ለዘለዓለሙም ከፍ ከፍ አድርጋቸው።


እኔ ከዓለም እንዳልሆንሁ ሁሉ እነርሱም ከዓለም አይደሉም።


“በይሁዳ ምድር የምትገኚ አንቺ ቤተልሔም፥ ከይሁዳ ገዢዎች ከቶ አታንሽም፤ ሕዝቤን እስራኤልን የሚጠብቅ መሪ ከአንቺ ይወጣልና።”


በዚያ ጊዜ የይሁዳና የኢየሩሳሌም ቁርባን እንደ ዱሮው ዘመንና እንደ ቀደሙት ዓመታት ጌታን ደስ የሚያሰኝ ይሆናል።


የእስራኤል ትሩፍ ኃጢአትን አይሠሩም፥ ሐሰትንም አይናገሩም፥ በአፋቸውም ውስጥ አታላይ ምላስ አይገኝም፤ እነርሱም ይሰማራሉ፥ ይተኛሉ፥ የሚያስፈራቸውም የለም።


አቤቱ፥ ወደ አንተ መልሰን እኛም እንመለሳለን፥ ዘመናችንን እንደ ቀድሞ አድስ።


ለፈለገኝ ሕዝቤ ሳሮን የበጎች ማሰማርያ፥ የአኮር ሸለቆ የላሞች መመሰግያ ይሆናል።


እጅግ ያብባል በደስታና በዝማሬ ሐሤትን ያደርጋል፤ የሊባኖስ ክብር፥ የቀርሜሎስና የሳሮን ግርማ ይሰጠዋል፤ የጌታንም ክብር የአምላካችንንም ግርማ ያያሉ።


የቀድሞውን ዘመን አሰብሁ፥ ሥራህንም ሁሉ አሰላሰልሁ፥ የእጅህንም ሥራ አስተዋልሁ።


እስራኤልም ተማምኖ፥ የያዕቆብም ምንጭ ብቻውን፥ እህልና የወይን ጠጅ ባለባት ምድር ይኖራል፥ ሰማያትም ጠልን ያንጠባጥባሉ።


በተራሮች ራስ ላይ ሆኜ አየዋለሁ፥ በኮረብቶችም ላይ ሆኜ እመለከተዋለሁ፤ እነሆ፥ ብቻውን የሚቀመጥ ሕዝብ ነው፥ በአሕዛብም መካከል አይቈጠርም።


እኔና ሕዝብህ በፊትህ ሞገስ ማግኘታችን በምን ይታወቃል? እኔና ሕዝብህ በምድርም ፊት ካለው ሕዝብ ሁሉ የተለየን የምንሆነው አንተ ከእኛ ጋር በመውጣትህ አይደለምን?”


ዛይ። ኢየሩሳሌም በጭንቀትዋና በመከራዋ ወራት ከጥንት ጀምሮ የነበረላትን የከበረን ነገር ሁሉ አሰበች፥ ሕዝብዋ በአስጨናቂዎች እጅ በወደቀ ጊዜ የሚረዳትም በሌላት ጊዜ፥ አስጨናቂዎች አዩአት በመፍረስዋም ሳቁ።


ከበሬም ሁሉ ከዐሥር አንድ፥ ከእረኛውም በትር በታች ከሚያልፍ በግና ፍየል ሁሉ ከዐሥር አንድ ለጌታ የተቀደሰ ይሆናል።


ወዳጄ ሆይ፥ እነሆ፥ ውብ ነሽ፥ እነሆ፥ አንቺ ወብ ነሽ፥ ዐይኖችሽ በመሸፈኛሽ ውስጥ ርግቦች ናቸው፥ ጠጉርሽ በገለዓድ ተራራ እንደሚወርድ እንደ ፍየል መንጋ ነው።


“ተነሡ፥ በደኅንነት ተቀምጦ ተረጋግቶ ወዳለው፥ የቅጥር በርና መቀርቀሪያ ወደሌለው ብቻውንም ወደ ተቀመጠው ሕዝብ ውጡ፥ ይላል ጌታ።


ሰውንና እንስሳም በእናንተ ላይ አበዛለሁ፥ እነርሱም ይበዛሉ ያፈራሉም፤ እንደ ቀድሞም ሰዎችን አኖርባችኋለሁ፥ መጀመሪያ ካደረግሁላችሁ ይልቅ መልካም አደርግላችኋለሁ፤ እኔም ጌታ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ።


የሮቤልና የጋድ ልጆችም እጅግ ብዙ እንስሶች ነበሩአቸው፤ እነሆም፥ የኢያዜር ምድርና የገለዓድ ምድር ለእንስሶች የተመቸ ስፍራ እንደ ነበረ ባዩ ጊዜ፥


ጌታ የእስራኤል ማኅበር እንዲወርሰው ያደረገው ምድር ሲሆን፥ ለእንስሶች የተመቸ ምድር ነው፤ ለእኛም ለባርያዎችህ እንስሶች አሉን።”


በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፤ ታላቅ መለከት ይነፋል፥ በአሦርም የጠፉ፥ በግብጽ ምድርም የተሰደዱ ይመጣሉ፤ በተቀደሰውም ተራራ በኢየሩሳሌም ለጌታ ይሰግዳሉ።


የደቡብም ሰዎች የዔሳውን ተራራ፥ የቆላውም ሰዎች ፍልስጥዔማውያንን ይወርሳሉ፤ የኤፍሬምንም አገር የሰማርያንም አገር ይወርሳሉ፥ ብንያምም ገለዓድን ይወርሳል።


ከግብጽም ምድር እመልሳቸዋለሁ፥ ከአሦርም እሰበስባቸዋለሁ። የሚበቃ ስፍራ እስኪጠባቸው ድረስ ወደ ገለዓድና ወደ ሊባኖስ ምድር አመጣቸዋለሁ።


እኔም ለእርድ የሚሆኑትን በጎች፥ የመንጋውን ችግረኞች ጠበቅሁ። ሁለት በትሮችንም ወሰድሁ፤ የአንዲቱን ስም “ደስታ” የሁለተኛይቱንም ስም “አንድነት” ብዬ ጠራሁ፤ መንጋውንም አሰማራሁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች