Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ማቴዎስ 9:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 “ልጅቱ ተኝታለች እንጂ አልሞተችምና ዞር በሉ፤” አላቸው። እነርሱ ግን ሳቁበት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 “ዞር በሉ፤ ብላቴናዪቱ ተኝታለች እንጂ አልሞተችም” አላቸው፤ እነርሱ ግን ሣቁበት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 እርሱም “ሁላችሁም ከዚህ ውጡ! ልጅትዋ አንቀላፍታለች እንጂ አልሞተችም!” አላቸው። እነርሱ ግን በማፌዝ ሳቁበት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 “ብላቴናይቱ ተኝታለች እንጂ አልሞተችምና ፈቀቅ በሉ፤” አላቸው። በጣምም ሳቁበት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 ብላቴናይቱ ተኝታለች እንጂ አልሞተችምና ፈቀቅ በሉ አላቸው። በጣምም ሳቁበት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማቴዎስ 9:24
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ጳውሎስም ወርዶ በላዩ ወደቀ፤ አቅፎም “ነፍሱ አለችበትና አትንጫጩ፤” አላቸው።


ጴጥሮስም ሁሉን ወደ ውጭ አስወጥቶ ተንበርክኮም ጸለየ፤ ወደ ሬሳውም ዘወር ብሎ “ጣቢታ ሆይ! ተነሺ፤” አላት። እርሷም ዐይኖችዋን ከፈተች ጴጥሮስንም ባየች ጊዜ ተቀመጠች።


ኢየሱስም ሰምቶ “ይህ ሕመም ለሞት አይሰጥም፤ ይልቁንም ለእግዚአብሔር ክብር መገለጫ ነው፤ የእግዚአብሔር ልጅ በእርሱ ይከብር ዘንድ ነው” አለ።


የተናቀ ከሰውም የተጠላ፥ የሕማም ሰው፥ ደዌንም የሚያውቅ ነው፤ ሰውም ፊቱን እንደሚያዞርበት የተናቀ ነው፥ እኛም አላከበርነውም።


የእስራኤል ታዳጊ ቅዱሱም፥ ጌታ፥ ሰዎች በሚንቁት ሕዝብም ለሚጠላው፥ ለገዢዎች አገልጋይ እንዲህ ይላል፦ ‘ስለ ታማኙ ስለ ጌታ ስለ መረጠህም ስለ እስራኤል ቅዱስ ነገሥታት አይተው ይነሣሉ፥ መሳፍንትም አይተው ይሰግዳሉ።’


ለባልንጀራው መሳለቂያ እንደሚሆን ሰው ሆኛለሁ፥ እግዚአብሔርን የጠራሁ እኔ፥ እርሱም የመለሰልኝ፥ ጻድቅና ፍጹም ሰው መሳለቂያ ሆኖአል።


ሰዎቹም ሳቁበት። እርሱ ግን ሁሉን አስወጣ፤ የልጅቱንም አባትና እናት እንዲሁም አብረውት የመጡትን አስከትሎ ልጅቱ ወዳለችበት ገባ።


እንደ ሞተችም ስላወቁ በጣም ሳቁበት።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች