ማቴዎስ 23:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)25 “እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን!ወዮላችሁ፥ የጽዋውንና የሳሕኑን ውጭ ታጠራላችሁ በውስጣቸው ግን ቅሚያና ራስን አለመግዛት ሞልቶባቸዋል። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም25 “እናንተ ግብዞች የኦሪት ሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን፤ ወዮላችሁ! የጽዋውንና የወጭቱን ውጭ ታጸዳላችሁ፤ በውስጣቸው ግን ቅሚያና ሥሥት ሞልቶባቸዋል። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም25 “እናንተ ግብዞች የሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን! ወዮላችሁ! ብርጭቆውንና ሳሕኑን ከውጪ በኩል ታጠራላችሁ፤ ውስጡ ግን ቅሚያና ሥሥት የሞላበት ነው፤ ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)25 “እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን! በውስጡ ቅሚያና ስስት ሞልቶ ሳለ የጽዋውንና የወጭቱን ውጭ ስለምታጠሩ፥ ወዮላችሁ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)25 እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ በውስጡ ቅሚያና ስስት ሞልቶ ሳለ የጽዋውንና የወጭቱን ውጭ ስለምታጠሩ፥ ወዮላችሁ። ምዕራፉን ተመልከት |