Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ማቴዎስ 18:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ባይሰማህ ግን አንድ ወይም ሁለት ከአንተ ጋር ውሰድ፤ በሁለት ወይም በሦስት ምስክር ቃል ነገር ሁሉ ይጸናልና፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ባይሰማህ ግን፣ ነገር ሁሉ በሁለት ወይም በሦስት ምስክሮች አፍ ስለሚጸና፣ አንድ ወይም ሁለት ሰው ይዘህ አነጋግረው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ባይሰማህ ግን የሁለት ወይም የሦስት ሰዎች ምስክርነት ስለሚጸና ሁለት ወይም ሦስት ሰዎች ይዘህ ወደ እርሱ ሂድ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ባይሰማህ ግን፥ በሁለት ወይም በሦስት ምስክር አፍ ነገር ሁሉ እንዲጸና፥ ዳግመኛ አንድ ወይም ሁለት ከአንተ ጋር ውሰድ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ባይሰማህ ግን፥ በሁለት ወይም በሦስት ምስክር አፍ ነገር ሁሉ እንዲጸና፥ ዳግመኛ አንድ ወይም ሁለት ከአንተ ጋር ውሰድ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማቴዎስ 18:16
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“በማንኛውም ወንጀል ወይም ሕግ በመተላለፍሰውን ጥፋተኛ ለማድረግ፥ አንድ ምስክር አይበቃም፤ ጉዳዩ በሁለት ወይም በሦስት ሰዎች ምስክርነት መረጋገጥ አለበት።


ወደ እናንተ ስመጣ ይህ ሦስተኛዬ ነው። “ማንኛውም ነገር በሁለትና በሦስት ምስክር አፍ ይጸናል።”


በሁለት ወይም በሦስት ምስክር ካልተደገፈ በቀር በሽማግሌ ላይ ክስ አትቀበል።


የሁለት ሰዎችም ምስክርነት እውነት እንደሆነ በሕጋችሁ ትጽፎአል።


የሙሴን ሕግ የተላለፈ ሰው “በሁለት እና በሦስት ምስክሮች ምስክርነት” ያለ ርኅራኄ ይሞታል፤


ሞት የሚገባው ሰው፥ በሁለት ወይም በሦስት ሰዎች ምስክርነት ይገደል፤ ነገር ግን በአንድ ሰው ምስክርነት ብቻ ማንም ሰው አይገደል።


ነፍሰ ገዳይ ሁሉ ምስክሮች በሰሚጡት ቃል ይገደላል፤ በአንድ ምስክር ግን ማናቸውንም ሰው መግደል አይገባም።


እነሆም፥ ነቢይ ወደ እስራኤል ንጉሥ ወደ አክዓብ ቀርቦ፦ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ‘ይህን ብዙ ጭፍራ ሁሉ ታያለህን? እነሆ፥ ዛሬ በእጅህ አሳልፌ እሰጠዋለሁ፥ እኔም እግዚአብሔር እንደሆንሁ ታውቃለህ’ አለ።”


ማቅ ለብሰው ሺህ ከሁለት መቶ ስድሳ ቀን ትንቢት እንዲናገሩ ለሁለቱም ምስክሮቼ ኃይል እሰጣለሁ።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች