Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ማቴዎስ 16:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ጠዋት ደግሞ ‘ሰማዩ ደምኖ ቀልቶአልና ዛሬ ይዘንባል’ ትላላችሁ። የሰማዩን ገጽታ መለየት ታውቃላችሁ፤ የዘመኑን ምልክት ግን መለየት አትችሉም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ንጋት ላይም፣ ‘ሰማዩ ቀልቷል፣ ከብዷልም፤ ስለዚህ ዝናብ ይዘንባል’ ትላላችሁ። የሰማዩን ገጽታ ትለያላችሁ፤ ነገር ግን የዘመኑን ምልክት መለየት አትችሉም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ሲነጋ በጠዋት ደግሞ ‘ሰማዩ ደመና ሆኖ ቀልቶአልና ዛሬ ይዘንባል’ ትላላችሁ፤ የሰማዩንስ መልክ መለየት ታውቃላችሁ፤ ነገር ግን የዘመኑን ምልክት መለየት አትችሉም።]

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ማለዳም ‘ሰማዩ ደምኖ ቀልቶአልና ዛሬ ይዘንባል’ ትላላችሁ። የሰማዩን ፊትማ መለየት ታውቃላችሁ፤ የዘመኑንስ ምልክት መለየት አትችሉምን?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ማለዳም፦ ሰማዩ ደምኖ ቀልቶአልና ዛሬ ይዘንባል ትላላችሁ። የሰማዩን ፊትማ መለየት ታውቃላችሁ፥ የዘመኑንስ ምልክት መለየት አትችሉምን?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማቴዎስ 16:3
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እናንት ግብዞች! የምድሩንና የሰማዩን ፊት ልትመረምሩ ታውቃላችሁ፤ ነገር ግን ይህን ዘመን የማትመረምሩ እንዴት ነው?


እስራኤልም የሚገባውን እንዲፈጽም የዘመኑን ሁኔታ የሚያውቁ ጥበበኞች ሰዎች የይሳኮር ልጆች አለቆች ሁለት መቶ ነበሩ፤ ወንድሞቻቸውም ሁሉ ይታዘዙአቸው ነበር።


ጌታም መልሶ እናንተ ግብዞች! ከእናንተ እያንዳንዱ በሰንበት በሬውን ወይስ አህያውን ከግርግሙ ፈትቶ ውሃ ሊያጠጣው ይወስደው የለምን?


ዕውሮች ያያሉ፤ አንካሶች ይራመዳሉ፤ ለምጻሞችም ይነጻሉ፤ ደንቆሮዎች ይሰማሉ፤ ሙታን ይነሣሉ፤ ለድሆችም ወንጌል ይሰበካል፤


እናንተ ወዮላችሁ! ሰዎች ሳያውቋቸው በላያቸው የሚሄዱባቸው የተሰወሩ መቃብሮች ትመስላላችሁና።”


“እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን! መንግሥተ ሰማያትን በሰዎች ፊት ስለምትዘጉ ወዮላችሁ፤ እናንተ ራሳችሁ አትገቡም፤ የሚገቡትንም እንዳይገቡ ትከለክላላችሁ።


ኢየሱስም ክፋታቸውን አውቆ እንዲህ አላቸው “እናንተ ግብዞች፥ ለምን ትፈትኑኛላችሁ?


እናንተ ግብዞች፥ ኢሳይያስ ስለ እናንተ እንዲህ ብሎ ትንቢት በትክክል ተናገረ፥


አንተ ግብዝ፤ አስቀድመህ በዓይንህ ያለውን ምሰሶ አውጣ፤ ከዚያ በኋላ በወንድምህ ዐይን ያለውን ጉድፍ ለማውጣት አጥርተህ ታያለህ።


ኢየሱስም በምኵራቦቻቸው እያስተማረ፥ የመንግሥትን ወንጌል እየሰበከ፥ በሕዝቡ መካከል ያለውን ደዌና ሕማም ሁሉ እየፈወሰ በገሊላ ሁሉ ይዘዋወር ነበር።


ጠንካራ ምግብ የሚያስፈልጋቸው ግን መልካሙንና ክፉውን የመለየት ልምድ ያላቸው ብስለት ያላቸው ሰዎች ናቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች